ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከጥቂት አመታት በፊት አክሱም ላይ ትንሽ ሃውልት ሰርቆ በጉያው አስገብቶ ለመውጣት ሲል አንድ አባት የያዙት የአንድ አውሮፓ ቤተ መዘክር አስተዳዳሪ ታሪክ ትዝ ይለኛል። ታሥሮ እንደነበር አስታውሳለሁ።
ትክክል ነው፤ ወደ አገራችን የሚጓዙትና እኛን የሚቀርቡን ነጮች ለእኛ በፍጹም በጎ ነገር አያስቡልንም፣ አያደርጉልንም። በእርግጥ እንደ መልአክ የሆኑ ነጮች አሉ፤ ነገር ግን ወደ እኛ የመቅረብ እድሉ የላቸውም፤ 90% የሚሆነው ነጭ ግን ለፀረ-ክርስቶሱ መንግሥት የተዘጋጀ ኤዶማዊ ነው፤ በመሪዎቹ በቀላሉ የሚነዳ ነው፡ የእኛ ጠላት እንዲሆን ተደርጎ የተኮተኮተ ነው፣ "የአፍሪቃውያን ድኽነት የእኛ ኃብት ነው፣ እነርሱ ኃብታም ከሆኑ እኛ እንደኽያለን" የሚለውን መርኾ ተቀብሎ የሚኖር ነው ።
ነጮቹም ቢሆኑ “ብሔራዊ” በሚሏቸው ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች ላይ አፍሪቃውያንን ማሳደር ቀርቶ፡ ለጉብኝት እንኳን አያስገቧቸውም። በየላብራቶሪው እንኳን፡ እራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ከሸጡት ወገኖቻችን በቀር፡ ጥቁሩን አስገብተው ለማሠራት ፈቃደኞች አይደሉም። ምስጢራት ናቸው የሚሏቸውን ነገሮች ለጥቁር ሕዝቦች አያካፍሉም።
ለምሳሌ፡ በጥቁር ሰው አካል ላይ በተፈጥሮ በብዛት እንድተቀበረ የሚነገርለትን “አምላካዊ የሜላኒን ቅመም” በተመለከተ በአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራሊያ በየዓመቱ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፤ ነገር ግን አንድም ጥቁር በስብሰባዎቹ ተካፍሎ አያውቅም። የኢሉሚናቲዎቹ የቢልደርበርግ ስብሰባም ጥቁሮችን ያገለለ ነው። በሌላ በኩል፤ በረጅሙ የጠፈር ምርመራ ታሪክ፡ ይህን ሁሉ ዘመን፡ አንድም “አፍሪቃዊ” ወደ ጠፈር ተልኮ አያውቅም፤ አንድም! ሁሌ ተፎካካሪዎች መስለው እርስበርስ የሚጠዛጠዙትና ለጦርነት የሚዘጋጁት አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያንና ሩሳውያን ጠፈር ላይ ቤት ሠርተው እስያዊውንና አረቡን እየጋበዙ በሕብረት “ምርምሮችን” ያካሂዳሉ። አፍሪቃውያን ግን አይጋበዙም፤ ለጠፈር ብቁ የሆነ አፍሪቃዊ ጠፍቶ ነውን? አይደለም!
የጣና ሀይቅ ገዳማት አባቶች ለሌላውም “ፈረንጅ አምላኪ” ወገናችን ትልቅ አርአያ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
Blogger Comment
Facebook Comment