፶ሺህ የዘንዶ መቅበሪያ ‘ቸርቾችን’ ለመሥራት ሲሉ ፡ ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን፡ ክርስቲያኖች በዓለም በጣም የሚበደሉባት 6ኛዋ ሃገር ነች አሉ



ሜሪላንድ ጋይርዶር ብሔራዊ ምርምር እና ስብሰባ ማእከል ፕሬዝደንት ትራምፕ መርቀው በከፈቱበት ዓመታዊው የአሜሪካ “ሲፓክ” Conservative Political Action Conference (CPAC) / ወግ አጥባቂ ፖለቲካ ተግባር ስብሰባ ላይ ነበር ትናንትና ይህን ተካፋዮቹ የተናገሩ ቀደም ሲል ክርስቲያኖች “በይበልጥ የሚበደሉባቸው አገሮችን” የሚመለከተው ስምዝርዝር የወጣው በግራክንፈኛው ግብዝ የፕሮቴስታንት „OPEN DOORS / ክፍት በሮች” ድርጅት ነው።

ይህ ድርጅት የክርስቲያኖች ጠበቃ ነኝ በማለት፤ ሁሌ በአንደኛ ደረጃ የሚያስቀምጠው ሰሜን ኮርያ ነው። ይህም በመላው ዓለም 95% ክርስቲያን በዳዮች የሆኑት የእስላም አገሮች ስለሆኑ ሰሜን ኮርያን አንደኛ በማድረግ የሙስሊሞችን ጭካኔ ለመሸፈን የተፈጠረ ተንኮል ነው።

ምክንያቱም፤ ሰሜን ኮርያ፦

1. የክርስቲያኖች አገር አይደለችም።
2. በሰሜን ኮርያ ተበደሉ የሚባሉት ቁጥራቸው በጣም ጥቂት የሆነ ፕሮቴስታንቶቹ ናቸው።
3. እነዚህ ፕሮቴስታንቶች ቢከፋ ቢከፋ ወደ እስር ቤት ይገባሉ እንጅ፡ በሙስሊሞች አገር እንደሚታየው ለግድያ አልተጋለጡም።
እና ነው።

ይህ ድርጅት ኤርትራን 6ኛ ኢትዮጵያን ደግሞ 29ኛ አድርጓቸዋል። በዚህም፡ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ቱርክና ሶርያ ይበልጥ ክርስቲያኖች በኤርትራና ኢትዮጵያ ይበደላሉ ማለቱ ነው። 

እስኪ እናስብ!
ሲፓክ (CPAC) (ቀኝ ክንፍ) ድግሞ ለፓነሉ በቀረበለት ጽሑፋዊ መረጃ ለክርስቲያኖች አስከፊ የሆኑት 10 አገሮች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
1. ሰሜን ኮርያ

2. አፍጋኒስታን
3. ሶማሊያ
4. ሱዳን
5. ፓኪስታን
6. ኢትዮጵያ
7. ኢራቅ
8. የመን
9. ኢራን
10. ህንድ

OPEN DOORS እንዳቀረበው ሳይሆን፡ በራሱ ፈቀድ በኤርትራ ቦታ ኢትዮጵያን 6 አድርጓታል። ይህም በስህተት ወይም ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ አይደለም፤ ሆን ተብሎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ላይ ያነጣጠረ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው። 

ስብሰባው ላይ የሚታዩት ፕሮቴስታንቶች (ባፕቲስቶች፣ ኤፒስኮፓሎች ወዘተ) ናቸው። እነዚህ አስመሳይ “ክርስቲያኖች” የጥንታውያኑ የመካከለኛው ክርስቲያኖች ተቆርቋሪዎች አይደሉም። ጥንታውያኑ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በግብጽ፣ ሶርያና ኢራቅ ጭፍጨፋ ሲካሄድባቸው ትንፍሽ አላሉም ነበር። እንዲያውም የጭፍጨፋው ተባባሪዎች ናቸው። አሁን እልቂቱ ከተፈጸመ በኋላ ተቆርቆሪ ሆነው መቅረባቸው ግብዝነት ነው።

አገራችንንም እዚህ ሰንጠረዥ ውስጥ ያስገቧት፣ ስሟን አጥፍተውና መንግስትን፡ እንደለመዱት “የሃይማኖት ነፃነት” ፣ “ሰብዓዊ መብት” ቅብርጥሴ እያሉ፡ በማስገደድ የአለሟቸውን 50ሺህ ፕሮቴስታንት ቸርቾች የተዋሕዶ ዓብያተ ክርስትያናት አጠገብ ለመገንባት በማቀድ ነው። ለዚህም ነው ሰርጎ ገቦችን እያዘጋጁ በተቻለ መጠን ስልጣኑን ፕሮቴስታንቶች ወይም እስላሞች እንዲይዙት የሚመኙት/ የሚያደርጉት። እንደነ አቶ አባዱላ (አብደላ) እና አቶ ደመቀ መኮንን የመሳሰሉትን።

እነዚህ ክርስቲያን ነን የሚሉ ድርጅቶች የተቀበሉትን ቃልኪዳን በመተው በ 500 ዓመታት ውስጥ በአውሮፓና አሜሪካ ክርስትናን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት የበቁ ድርጅቶች ናቸው። ታዲያ አሁን ከእኛ ጋር አብረው ወይም ከእኛ እርዳታ ጠይቀው ነፍሳቸውን ለማዳን እንደመሞከር፣ እንዲያውም ያልተነካውን ድንግል ነፍስ አድኖ ለመብላት ወደ እናት ኢትዮጵያ ይጎርፋሉ። 

ታዲያ ይህ የአውሬዉ ዘንዶ መንፈስ አይደለምን?!
ግራኞቹም ቀኞቹም አታላዮች ናቸው
[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ፳፯]
ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ።
[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፩፲፭]
ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment