UNESCO 50% የምድራችን ህዝብ ግብረሰዶማዊ የማድረግ እቅድ አለው


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ



የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) በመጪዎቹ 20 ዓመታት 50% የሚጠጋውን የዓለማችንን ነዋሪ ግብረሰዶማዊ የማድረግ ዕቅድ አለው። ዩኔስኮ የተለያዩ መርሐ ግብሮች በመከተል ማህበረሰቦች ተፈጥራዊ የሆነውን መሠረታዊ የጾታ አመለካከት በመቀየር በተለይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ግብረሰዶማዊነት መጥፎ የሆነ ድርጊት እንዳልሆነ ለማስተማር አቅዷል። ይህ ዘዴ በተደጋጋሚ በዚህ ድረ-ገጽ ገልጬዋለው።

ይህን መሰሉ ሁኔታ አዲስ ባይሆን አሁን “ሰለጠነ” በሚባለው ዓለም እየተፈጠረ ያለው ክስተት ምናልባት በዓለማችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ክስተት ነው። ጠቢብ ነው የተባለው ወገን መጥፎ ድርጊቶችን በመፈጸምና በኃጢአት በመሰልጠን ከፈጣሪው ለመራቅ ቆርጦ ተነስቷል። የሰዎችን ህሊና በመቆጣጠር ብሎም የሕሊና ህወከትን ፈጥሮ የቀረውን የሰው ልጅ ወደ ዲያብሎስ ቅጥር ግቢ ለመጨመር የሚታገለው የሕሊና ፖሊስ፥ ጦርነት ሰላም ባርነት ነፃነት ግድየለሽነት ብርታት እንደሆነ ባጠቃላይ ኃጢአት ጽድቅ ጽድቅ ኃጢአት እንደሆነ ሊያሳምነን እየሞከረ ነው።
በሃገራችን ኢትዮጵያም በበጎ አድራጎትና እርዳታ ስም የሚገቡት እንደነ ኤስ.ኦ.ኤስ (SOS) ፣ ሴቭ ዘችልድረን(Save The Children) ዩ.ኤስ.ኤይድ (USAID) መሰል ራሳቸው መንግሥታዊ አይደለንም የሚሉ ድርጅቶች ግን የኢሉሚናቲ ሰይጣናዊ ዕቅድ አስፈጻሚዎች የሆኑ  ይህንን ርኩስ የግብረሰዶማዊነት ተግባር በንጹሓን ኢትዮጵያውያን ህጻናት የሚተገብሩና የሚያስፋፉ ናቸው።
ልብ ብሎ ላስተዋለ፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ከፈጣሪው የተሰጠውን ነጻ ፈቃድ ያላግባብ በመጠቀም ተፈጥሮን የሚጻረሩ ድርጊቶች መፈጸም ከጀመረ ቆይቷል። ሰለጠኑ በሚባሉት የአውሮፓ፡ እስያና አሜሪካ ግብረሰዶማውያን ሕጋዊ እውቅና እየተሰጣቸው ነው፡ ወንዶች ከወንዶች፡ ሴቶች ከሴቶች ጋር እንዲጋቡ እየተፈቀደላቸው ነው። ክርስቲያኖች በተለይ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምሕርት የሚከተሉት ኢትዮጵያውያን ግብረሰዶማዊነትን አጥብቀው ስለሚያወግዙ በዓለማችን በመታየት ላይ ያለውን የእኩልነት ወረርሽኝ በሽታ የሚያስፋፉት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሊዋጓቸው በቆራጥነት ተነሳስተዋል። ማንነታችንን አጠንቅቀው የሚያቁትም እነዚህ ሃይሎች ሊበድሉን፡ ሊለዩን ሊያጥላሉንና ሊገድሉን እንደተዘጋጁ ሁላችንም የምናየው ነው።
እንግሊዝ አገር ውስጥ ለሁለት ግብረሰዶማውያን ወንዶች የሆቴል ክፍል አልሰጡም የተባሉ ክርስቲያናዊ ባለቤቶች በግብረሰዶማውያኑ ተከሰው ፍርድ ቤትም “ፀረ–አድሎ” የሆነውን ሕግ ጥሳችኋል በማለት የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ተሰጥቷቸዋል።

ሆሊውድም ብዛት ባላቸው ፊልሞቹ የግብረሰዶማውያንን አጀንዳ የሚያራምዱ ፊልሞች በማውጣት ላይ ነው። ለምሳሌ ለመጥቀስ ሮበርት ዲኔሮ ደስቲን ሆፍማን ጀሲካ አልባ እና ቤን ስቲለር የሚታዩበት “‘Little Fockers’…የተሳተፉበት ሦስተኛው የ “ቤተሰቦችን ተዋወቁ” ተከታታይ ፊልም ላይ መጥቀስ የማይስፈልገው አጸያፊ ግብረሰዶማዊ ተግባር በአንድ የጥቁር አክተር አማካይነት በሆስፒታል ውስጥ ሲካሄድ ይታያል። ማናቸውም በሰውነት ውስጥ ጠልቀው የሚገቡ ድርጊቶች ግብረሰዶማዊ የሆነ ባሕርይ የያዙ ናቸው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ይህን ፊልም ለማየት የእድሜ ገደብ አለመኖሩ ነው፡ ሕፃናት ሁሉ ማያት ይችላሉ ማለት ነው። ስንቶቻችን እንሆን በዚህ ኤፒዞድ ከተመልካቹ ጋር አብረን ስንስቅ የነበርን?

አውሬው: የሰውን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት ከሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች አንዱ ይህ ግብረሰዶማዊነት ነው። ይህን ድርጊት ለማስፋፋት በቅድሚያ ተለምዷዊ የሆነውን ጠንካራ የማሕበረሰባዊ ኑሮ ማናጋት ነው። ለዚህም የአንድ ህብረተሰብ ምሰሶ የሆነውን የቤተሰብን መዋቅር ማናጋት የግለሰቦችን ብሎም የህዝቦችን ማንነት የሚገልጹትን እንደ እምነት ፣ ባሕልና ቋንቋ የመሳሰሉትን ድንቅ ሥራዎች ለማጥፋት ሃይማኖታዊ ተቋማትን  ፣ ድርጅቶችንና መንግሥታትን ሁሉ መፈታተን ነው።

ከፈጣሪአችን ጋር ጽኑ በሆነ እምነት ከተሳሰሩት ጥቂት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። የኢትዮጵያ ተዋህዶ ክርስትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ዕምነት ፣  መንፈሥ  ፣ ባሕል  ፣ ቋንቋና ስነጽሑፍ ላይ እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ ሚና ስለምትጫወት ለዘመናት ዲያብሎስ በገሃድ ሆነ በድብቅ ሲፈታተናት ኖሯል። ምንም እንኳን እስከ መጨረሻው መጽናት ያቃታቸው ደካማ ወገኖች ማንነታቸውን በመካድ በዲያብሎስ እጅ ሥር ለመግባት ቢበቁም የኢትዮጵያ ክርስትና ኃይል ጠላቶቿን ሁሉ እየገረሰሰች እስካሁን ድረስ ለመቆየት በቅታለች፤ ለወደፊቱም የዲያብሎስን ሴራ እያጋለጠች ለደከመው የዓለማችን ክፍል ሁሉ አርአያ ለመሆን እንደምትበቃ የማያጠራጥር ነው፤ እግዚአብሔር ክርሷ ጋር ነውና።

ባዕዳን ፀረ–ኢትዮጵያ ኃይሎች፡ ከኢትዮጵያ ተወላጆች ከሃዲዎች ጋር በመመሣጠርና በመተባበር፡ ምድረ ኢትዮጵያን ከመዋጋት ወድኋላ አይሉም። በረሃብ፡ በበሽታና በጦርነት ሕዝቡን ለማድከም ብሎም ቁጥሩን ለመቀነስ ስላልተቻላቸው፡ ለግበረሰዶማዊነት አመቺ የሆኑትን የአኗኗር ዘይቤዎች ቀስበቀስ ወደ አገራችን በማስገባት ላይ ይገኛሉ። እንደ ዩኔስኮ (UNESCO) ፣ ዩኒሴፍ (UNICEF) ፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንዲሁም ቀይመስቀልን የመሳሰሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካሎች መንግሥታዊ ካልሆኑ ዓለምዓቀፋዊ ከሆኑ ድርጅቶች ብሎም እንደ ፔንቲኮስታል እና እንደ ዋሀቢ እስላም ከመሳሰሉ የርዕዮት ዓለም ፋብሪካዎች ጋር በመተባበር ሰይጣናዊ ውጊያቸውን በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህን ዲያብሎሳዊ ዘመቻቸውን እንደዱሮው ከውጭ ሆነውና ባዕዳውያንን ብቻ በመጠቀም ሳይሆን የሚያካሂዱት፡ በውስጣችን ሰርገው በመግባት እና ከእኛ የወጡትን ወይም እኛን የመሰሉትን ከሃዲዎች በመመልመል ነው። አዲስ አበባችን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማዕከል መሆኗ መልካም የሚሆነው፡ እነዚህ ከተማይቱ የምታስተናግዳቸው ድርጅቶች የሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጆች አገልጋዮች ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች  ኢትዮጵያና ኤርትራ በሚሉ ሁለት አገሮች ለመከፋፈል የበቁት፡ እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠሩ የሩዋንዳ እና የደቡብ ሱዳን “ኢትዮጵያውያኖች” አሰቃቂ በሆነ መልክ ለመጨፍጨፍ የበቁት እንደ ቦትሮስ ቦትሮስ ጋሊ እና እንደ ኮፊ አናንን የመሳሰለቱ ከሃዲ “አፍሪቃውያን” የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊዎች ሆነው ከተሾሙ በኋላ ነው።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር የሚገኝው ዩኔስኮ(UNESCO) የሃገራችን ቅርሶች የሚመዘግበው ለበጎ ምግባር አይደለም። የተለያዩ አረማውያንና ባዕዳን ሰዎች በቅዱሳን ቦታዎች ተገኝተው መንፈሳዊ ሃብቶቻችን እንዲመዘብሩና የርኩሰት ተግባራቸው እንዲፈጽሙበት በር ለመክፈት እንጂ።

ይህ ሁሉ የምዕራባውያን የርኩሰት ተግባር ግን ለረጂም ጊዜ የሚዘልቅ አይደለም። ሀገረ እግዚአብሔር የሆነቺው ኢትዮጵያ  ትንሣዔዋ በእውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ ባርያዎች ተረጋግጦ የመሪነትና የአስተዳደር ስልጣኑ ሲረከቡት ከሃዲዎችና የዓመጻ ልጆች ቦታ አይኖራቸዉም። ይህም በቅርቡ የሚሆን ነው። ብቻ በተስፋና የኢትዮጵያ አምላክ በእውነተኛ መንፈስ በማምለክ ጸንተን እንጠብቅ።

በስተመጨረሻ ሳልገልጽ ማለፍ የማልፈልገው በአዲስ አበበ መካነ አዕምሮ (Addis Ababa University) ሥር የሚንቀሳቀሰው Yellow Movement ‹‹ የሴቶች መብተ ተሟጋች ነኝ! ›› የሚል ስብስብ ቢሆንም የግብረሰዶማውያን ሴቶች ( Lesbian) ስብስብ ነው።  "የሴቶች መብት ተሟጋች"  የሚል ጭንብል ነው።

‹‹በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉ ና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።››
---የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯ ፥ ፳፮ ፡ ፳፯


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment