የማንቅያ ደወል ለቅድስት ሃገር ልጆች ኢትዮጵያውያን


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

እኛ በዲያብሎስ የፖለቲካ ገመድ እርስበርሳችን ስንጠላለፍ ጥንተ ጠላቶቻችን ምዕራባውያን በኛ ላይ የሚያሴሩት የጥፋት ስራ እየሰሩ ነው። ስለ ኢሉሙናቲ ሴራ ስጽፍ ስታሾፍና ስትቀልድ የነበርክ ሰው አሁን ንቃ።

የእህተ ማርያም ኃይለኛ መልዕክት | ወሊድ መከላከያ የምትጠቀሙ ከሆነ 666 ዘንዶውን/ አውሬውን ለመከተል በፈቃዳችሁ መርጣችኋል ማለት ነው

"ወደ ቤ/ክርስቲያን መግባት አትችሉም፣ ሥጋውንና ደሙን መቀበል አትችሉም፣ መጠመቅ አትችሉም፤ የእየሱስ ክርስቶስና የእናቱ የቅማርያም ልጆች ነን ማለት አትችሉም።"

ይህ የእህታችን ሌላ ታላቅ ትምህርት ነው። የተቀበለችው መረጃ ለአገራችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት መረጃዎች መካከል አንዱ ነው። ይህን መረጃ ዓብያተክርስትያናቱ በየዕለቱ ሳራችን ብለው በሰበካዎቻቸው ወቅት ደግመው ደጋግመው ሊናገሩልት ይገባል።
እህቶች እባካችሁ የወሊድ መከላከያውን በጭራሽ አትጠቀሙ፤ ለማስወረድማ የምታስቡት ጉዳይ አይደልም” ብለው በየቀኑ መናገር ይኖርባቸዋል። ግማሽ ደቂቃ እንኳን የማትወስድ አንዲት ዓረፍተ ነገር ናት።
666ቱ አውሬ ጋር የተመሳጠሩት ሜዲያዎች ባዕዳውያኑ የወሊድ መከላከያና ህጻናት ገዳይ ድርጅቶች ማስታወቂያ ይሠራሉ እንጂ ለእህቶቻችን ማስጠንቀቂያ ሊሰጡ ፈቃደኞች አይደሉም። አቤት ጉዳቸው!
ከ 7500 አመታት በላይ ትክክለኛው አምልኮተ እግዚአብሔር የምትፈጽመው ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር በመመረጥዋና የእግዚአብሔር ጥበቦች መገኛና ማስፈጸምያ በመሆንዋ በተለያዩ ጊዜያት ይህንን የሚያውቁ ባዕዳውያን ሃይሎች ወደ ሃገራችን በመምጣትና በርቀትም ጥበብዋን ለመዝረፍና ጥንታዊው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖትዋን ለመበረዝ የተለያዩ የሰይጣን አምላኪዎች የሆኑ የምስጥር ማህበራት ጥረት አድርገዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃ እስከ አሁን ብት ዘልቅም አውሬው(666) ግን ተቃውሞውና ሴራው ለማስፈጸም እስከ መጨረሻ እንደሚጥር የታወቀ ነው።
ልብ ብለን እንከታተል፦ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት አሁን መምረጣቸው ያለ ምክንያት አይደለም። ያቀዱት ትልቅ ሴራ በመኖሩ ነው። አቶ ቴዎድሮስ አድሓኖም ከመመረጣቸው በፊት የተጻፈ ጽሑፍ ዝርዝር መረጃ አስፈንጣሪው በመጫን ያንብቡ።

የህዝባችንን ቁጥር በጦርነት፣ በርሃብ፣ በበሽታ፣ በ HIV ኤድስ ሊቀንሱት አልቻሉም፤ ስለዚህ አሁን የመጨረሻው ጦርነት ላይ ገብተዋል፤ በዚህም ሁለት ወፍ በአንድ ድንጋይ ለመምታት ቆርተው ተነስተዋል፤ ይህም፦ ቁጥሩን መቀነስ እንዲሁም የሚወለዱትን በአውሬው መንፈስ ቁጥጥር ማስገባት።

ማሪስቶፕስ ስለ ሚባለው የሰነ ተዋልዶ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሴራ ለማንበብ ተከታዩ አስፈንጣሪ ይጫኑ።


ባካችሁ፣ ባካችሁ የወሊድ መከላከያ አትጠቀሙ፣ ህጻናቱንም መርፌ አታስወጉ። እስኪ ወሊድ መከላከያ ለምን እንደምትጠቀሙ እራሳችሁን ጠይቁለማመንዘር አይደለምንእስኪ የተረገዘውን ለምን እንደምታስወርዱ እራሳችሁን ጠይቁግድያ አይደለምንበእነዚህ ድርጊቶች ብቻ ሙሉውን የእግዚአብሔርን አሠርቱ ትዕዛዛት እያወቃችሁ ሽራችኋቸዋል፤ ከእየሱስና እናቱ ጋር በጽኑ ተጣልታችኋል ማለት ነው። ከዚህ የበለጠ አስከፊ ነገር ይኖራልን?
  1. እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፡፡ ዘጸ 202-3፡፡
  2. የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ ዘጸ 207፡፡
  3. የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ አክብረውም፡፡ ዘጸ 2010፡፡
  4. አባትህንና እናትህን አክብር፡፡ ዘጸ 2012፡፡
  5. አትግደል፡፡ ዘጸ 2013፡፡
  6. አታመንዝር፡፡ ዘጸ 2014፡፡
  7. አትስረቅ፡፡ ዘጸ 2015፡፡
  8. በሐሰት አትመስክር፡፡ ዘጸ 2016፡፡
  9. አትመኝ፡፡ ዘጸ 2017፡፡
  10. ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡ ዘሌ 1918፡፡
ይህ ኢትዮጵያና ተዋሕዶ ሃይማኖቷን ለመለወጥና ለማጥፋት የሚደረግ ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅል እንደማይወስዳቸው ያውም ኢትዮጵያዊነታቸውን በካዱት ግለሰቦች ድጋፍ ተጨምሮበት እውን ለማድረግ መጣራቸው ግልጽ ነው።
ሰብዓዊነተቻችንና ማንነታችንን ለማጥፋትና ደካማውን የምዕራባውያንን ባዕዳዊ እምነትን በሕዝባችን ላይ ለመጫን የአውሬው ሠራዊት የሚያደርገውን ጥረት ሁሉ መቃወምና እግዚአብሔር የሰጠነንን ልዩ ማንነት መጠበቅ ይገባናል።

 ዓርብ  የካቲት 16., 
2010 ዓመተ ምሕረት



Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment