"ከኢራን ጎን እንቆማለን" ሼክ ኢብራሂም ቱፋ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ መሪ ላይ የደረሰውን ህልፈት ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ በመገኘት የሃዘን መግለጫ ሰጥተዋል።

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኤምባሲው ተገኝተው የሃዘን መዝገብ ላይ የፈረሙ ሲሆን በወቅቱም ባስተላለፉት መልዕክት በደረሰው ጥቃት መሪው በሰማዕትነት ማለፋቸው ለመላው የኢራን ህዝብና መንግስት ታላቅ ሃዘን መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢራን ወንድሞቻቸው ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

ይህ ህልፈት ለኢራን ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ሙስሊሞች ትልቅ ኪሳራ መሆኑን ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

መረጃው የኢራን ኤምባሲ ነው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment