ሥውሩ መነኩሴ [ክፍል ፪]


✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

....ስንት ስአት ነበር ወደዚህ የመጣችሁ? አሉ መጋቢው ሰዓት እንኳ አላየሁም። ነገር ግን መንገድ የጀመርነው ጸሐይዋ ከመግባቷ ነው ቢያንስ የሁለት ሰአት የእግር መንገድ ተጉዘን ይሆናል...ዳገቱን በስተቀኝ ትተን በጥቅጥቁ ደን ውስጥ ነበር የመጠነው።

መጋቢው እጃቸውን አፋቸው ላይ ጭነው በመገረም በጫካው በኩል ነው እንዴ አልፋችሁ የመጣችሁ? ጭንቅላታቸውን በመወዝወዝ ሃዘን መሳይ ግርምታቸውን ገለጡት።

ሁኔታቸውን ተመልክቸ ምነው አባቴ ምነው ችግር አለ?
መጋቢው ግን እያዳመጡኝ አልነበረም በነገርኳቸው ነገር ተገርመው አእምሯቸው የፈጠረባቸው ጥያቄ ጋር ትግል የገጠሙ ይመስላሉ።

እስኪ የሆነ ቦታ ደርሼ ልምጣ ብለው ከአለቱ ላይ ያስቀመጡትን የመነኩሴ ፎጣ በስርአቱ ተላብሰው ሄዱ።

የሆነ ህልም ውስጥ የምዋዥቅ መሰለኝ እየሆነ ያለውን እውነት ከመረዳት ይልቅ ምህታትዊ ምዕናብ ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኛል። በእርግጥ በሂወቴ በርካታ ገዳማት ዙርያለሁ፣ ብዙ እውቀትንም ተካፍያለሁ፣ የተለያዩ አስደናቂ የአኗኗር ዘየወች፣ የአበው የገዳማት የአምልኮ ስርአቶችንም ተመልክቻለሁ፣ አለም ላይ ተጽኖ ፈጣሪ የነበሩ አለማውያን ራሳቸውን ለፈጣሪ አስገዝተው በምንኩስና ስርአት ሂወታቸውን ሲመሩ በተረጋጋ ሁኔታ ገዳማዊ ሂወታቸውን ሲያስኬዱ ተመልክቸ እጹብ እጹብም ብያለሁ።

በማያገባኝ እየገባሁ በማይ'ገባኝም እየዘባረኩ ሂወቴን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ክስተቶችም ገጥመውኝ በእግዚአብሔር ቸርነት አልፌያለሁ። 

የተዘዋወርኩባቸው ቦታወች እጂግ በርካታ ልዩነት ቢኖራቸውም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር የመነኮሳት ሂወት፣ ማንነት፣ እና ጥበባቸው፣ እጂግ የተሰወር ሚስጥራዊ መሆኑ ነው።
#ከዚህ_ቦታ ላይ የገጠመኝ ነገር መድረሻ ሆነ መጀመርያው ያልተገጠ የተቆላለፍ ነገር መሆኑ ግን ግራ አጋብቶኛል።...
ከተቀመጥኩበት አይኖቸን ወደተለያየ አቅጣጫ ስወረውር ከመጋቢው ቤት ራቅ ብለው ሁለት መነኮሳት አጥራቸውን ያጥራሉ። በዝግታ ወጣሁና ወደ እነርሱ ተጠጋሁ ከወገቤ ጎንበስ ብየ ሰላምታን አበረከትኩ በአጸፋው ጎንበስ ብለው ሰላምታየን መለሱ ፈጠን ብየ ሄጄ ጫፍና ጫፍ ለሁለት የተሸከሙትን የተቆረጠ የፓፓያ ግንድ ተቀበልኳቸው።

እጂግ የደከሙ መነኮሳት፣ አይኖቻቸው የፈዘዙ፣ አካላቸውን እንኳ በቅጡ መሸከም የማይችል ተክለ ሰውነት፣ ገላቸውን ሙሉ መሸፈን ያልቻለ የተቀዳደደ ቀሚስ፣ እድፍ ያለች አስኬማ አድርገው ጎንበስ ቀና ይላሉ።

ልቤን ሰበሩት የእውነት ያጡ የነጡ ድሆች ስለሆኑ ለሰወነታቸው ልብስ፣ ለእግራቸው ጫማ፣ ኑሮ የነፈገቻቸው መሰለኝ.... ሁኔታቸውን በትኩሮት ስመለከት ስለ እኛ እያሰብክ ነው ልጂ አሉኝ አንደኛው ጠየም ብለው ኑሮ ያጎበጣቸው መነኩሴ። ልቦናየን ያነበቡት እስኪመስለኝ ተርበተበትኩ። ልክ እኮ ነህ ያው... ታድያ ተየት መጣህ? የተለመደ የመነኮሳት ጥያቄ ነው ትንሽ ራቅ ይላል ብየ የመጣሁበትን አስረዳሁ....በያዙት የብረት አንካሴ ለአጥር የሚሆን ገደል ሲቆፍሩ ከተቀመጥኩበት ፈንጠር ብየ በመነሳት ላግዝወት ላግዝወት አይ አይ እንግዳ ክቡር ነው አሉ እንደምንም ተቀብየ ቁፍሮ ስጀምር እስቸው እንዳሰቡት ስፋትና ጥልቀት መቆፈር ተሳነኝ ቆይ ልጂ ቆይ እንዲህ ነው ብለው ከዚያ ከደከመ ገላ የማይታመን በጎረምሳ ምት ቆፈሩት.... ደካማ ሲሏቸው ጠንካራ ሁነው ተገኙ። መኖር ባልችል እንኳ ስለ ቀደመ ኑሮወቻቸው መጠየቅ፤ ስላለፈ ታሪካቸው መስማት፤ ከኖሩት ኑሮ መካፈል፤ ከገጠመኖቻቸው ገጠመኖች ማድመጥ፤ ከሂወታቸው ሁሉ መማር፤ ከመነኮሳቱ ዘንድ ልምዴ ነውና ከባዕታቸው ቁጭ ብየ ለኑሮ ምግብ፣ ለሂወት ስንቅ፣ የሆነኝን ምክርና ተግሳጽ ተቀበልኩ። ይንንም ኑሮ ወደውት እና ፈልገወት እንጂ አጠተው እንዳልመረጡት ገባኝ። ስለ ሰማያዊው ልብስ ሲሉ ምድራዊ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ስለ ሰማያዊ መንግስቱ ሲሉ ምድራዊ ክብራቸውን አዋረዱ።...

ከህይወታቸው ኑሮን ዘግኘ ክብር ሰላምታን ሰጥቸ ስወጣ ከኋላየ ወልደፃድቅ አሉኝ ''በእርግጥ እኛ ገዳዮቻችን ይምጡልን እንላለን ነገር ግን ይህ ዘመን ለቀሪወች.... እግዚአብሔር ከእናነተ ጋራ ይሁን ሰላም ሁኖ ድጋሚ ከተመለስክ ዛዕቲ ይዕቲ መካንየ(ያች ነች ቦታየ)'' ብለው በያዟት እንጨት ወደ ለመለመች ተክል አመለከቱኝ... ።

ጥያቄ ለማቅረብ ፋታ ሳይሰጡኝ ወጡ.. ምን ለማለት እንደፈለጉም ሳልረዳ እኔም ቀድሞ ሲያሳስብኝ ወደ ነበረው ጉዳየ ተመለስኩ።

እየተዘዋወርኩ በዙሪያው ያሉ እጽዋቶችን ስመለከት ቆይቸ ከትልቅ ዋርካ ስር ካለው ባርጩሜ ቁጭ ብየ አይኖቸን በየ አቅጣቸው ስልክ አንድ ትኩረቴን የሳበኝ ነገር ተመለከትኩ።

ከአራት በአራት በሆነች የጭቃ ቤት የወጡ በነጭ ወረቀት ላይ ቁመዉ የሚሞነጫጭሩ ደንደን ያለ ተክለ ሰውነት ጠይም ገጽታ ያላቸው መንኩሴ በግራ እጃቸው ወረቀት በቀኝ ደግሞ አስክርቢቶ እንደያዘ ቁልቁል ወረዱ.....

#አዲስ_ነገር ፈላጊነቴ ከተቀመጥኩበት አርጩሜ እምር ብየ በመነሳት ከእርምጃ በፈጠነ ከሩጫ ዝግ ባለ አጓጓዝ ደረስኩ። ገረበብ ባለችው በር አጮልቄ ስመለከት ከጫፍ እስከ ጫፍ የተዘረጋ ጥቁር ሰሌዳ በጂኦሜትሪ ስእሎች ሞልቶ ተመለከትኩ..። 

ጠይሙ መነኩሴ ምን ሊሰሩ እንዳሰቡ ባልረዳውም ግን በሳይንስ ዘንድ ብቁ የሆኑ ሰው እንደሆኑ ተረዳሁ።

ወደ ወረዱበት ቁልቁል መንገድ ተከትየ ወረድኩ፤ ከሲሚንቶ ኮንክሪት የተሰራ የሚመስል እጂግ ማራኪ የሆነ ተራውን የተደረደሩት ከኖራ አፈር የተገነቡ ቤቶችን ተመለከትኩ። ሰላምታየን ስሰጥ በፈገግታ ተቀበሉኝ..እጂግ የሚያምሩ የሲሚኒቶ ቤቶችን የሚያስንቁ ስራወች ናቸው ስል በፈገግታ ''ስራቸን ከአፈር መሆኑን አሳበቅክ'' አሉኝ ምሁሩ መነኩሴ።

''አለም እንዴተ ሰንበታለች? ምን አዲስ ክስተት አለ? አሉ በእጃቸውን ህንጻውን እየነካኩ''...አለም አሰልች ነች... በምንኖርባት ምድር ሁሉም ነገር እየተለወጠ ነው ለውጡ ለበጎ ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን ሰው ሁሉ ሰባእዊ ባህሪውና ጠባዩ እየተለወጠ ነው ይህ ደግሞ አደጋ ነው ህዝቡ በፍርሃት ቆፍን ውስጥ ወድቋል...አልኳቸው።

ወደ ቤታቸው እያመራን ፈገግ የሚያስብሉ ነገሮችን እያወጉኝ በጂኦሜትሪ የተመላችውን ቤት በስተቀኝ ትተን ወደ ባዕታቸው ተጓዝን።

ከሁሉም ባዕቶች ራቅ ብላ ለብቻ የተሰራች ውብ በኖራ የተቀለሰች ቤት የእሳቸው የእጂ ስራ መሆኗን አይቸ ተረዳሁ....። በሃርግ አጥር የተከለለው ቤታቸው በጀርባ በኩል ታላቅ ጋራ ታክኮ በግራና ቀኝ ደግሞ ሚያማምሩ እጽዋቶች ተውቧል። በቦታ አመራረጣቸው ተገርሜ በሃርግ አጥር የተከበበችውን ጎጆ ስዞር ከጋራው ጫፍ እስከ ጫፍ የተወጠረ አቦጀዴ የሚያማምሩ ስነ ስእላትን በአግርሞት ተመለከትኩ። የእያንዳንዱ ስእል ላይ የውይን ሃረግ ፍሬ የመሰሉ ስአላት በተሰጣቸው የቁጥር ውክልና ተቀምጠው አየሁ ስእላቱ ላይ ያየሁት ፍሬ የአባ ገ /ሂወት ከትራሴ ላይ ጥለዋት የሄዱ አይነት ስትሆን የለመለመች የእጽዋት ቀጥሏም '' ዛእቲ ይእቲ መካንየ'' ያች ነች ቦታየ ብለው መነኩሴው የተቆሙኝ ነች.....የነገሮቹ መገጣጠም ወደ አንዳች ጫፍ ይወስደኝ ይሆን.....

የመጨረሻውን ክፍል ይቀጥላል..
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment