በቴክኖሎጂ ያደገች፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች፣ ዜጎቿን ከድህነት ነፃ የወጣች ሀገር ለምን አልሆነችም?
እስኪ ለዚህ ጥያቄ መልሱን እንፈልግ። ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ቁጭ ብለን እናስበው፣ እናሰላስለው እስኪ።
የሀሳባችንን መንገድ በዚህ ጥያቄ እንጀምር፦ ለመሆኑ እኛ ማደግ እንችላለን? በቴክኖሎጂ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ፣ ትልልቅ ነገሮችን መስራት እንችላለን?
አንዳንድ ሰው፣ ለዚህ ጥያቄ "አይ አንችልም፣ ጥቁሮች ስለሆንን ጥቁሮች ምንም ሰርተው አሳይተው ስለማያውቁ ተስፋ የለንም" ብሎ ሊመልስ ይችላል። በመልሱ ባንስማማም እንዲህ የሚሉ ሰዎች ከምን አንግል እንደሚሉት መረዳት አይከብድም። በዓለም የድህነት ጥግ ላይ ያለነው እኛ ጥቁሮች ብቻ ነን። ሌላው ኤሺያ አረቡ ላቲን አሜሪካው ሁሉ በየአቅሙ አድጓል ከኛ የተሻለ ደረጃ ላይ ነው። በአፍሪካ እንኳ ሰሜን አፍሪካውያን እንደኛ ጥቁር ያልሆኑት የተሻለ ኢኮኖሚ እና እድገት አላቸው። እኛ ግን ከነሱም ተነጥለን "sub-saharan Africa" የሚል ስም ተሰጥቶን፣ የዓለም የድህነት፣ የረሃብ እና የኋላ ቀርነት ምሳሌ ተደርገን አለን።
ስለዚህ ጥቁርነታችን አንዳች መርገምት ሆኖብን ይሆን? መስራት እንዳንችል የገደበን እሱ ነው?
መልሱ አዎ ከሆነ፣ ይህንን ንግግር (discourse) የምንቀጥልበት ምክንያት የለም። በቃ እጣ ፈንታችን ነው ብለን ርዕሱን ዘግተን፣ ተስፋም ቆርጠን ማለፍ ነው።
ነገር ግን መልሱ "አይደለም" ነው። እንዴት አይደለም? የሚለውን ማየት ከቻልን ሀሳባችንን መቀጠል ያስችለናል።
እኛ ኢትዮጵያውያን ጥቁሮች ብንሆንም፣ ግን በመላው ታሪካችን ነገሮችን ሰርተን በማሳየት ነው የምንታወቀው። አክሱም፣ ላሊበላ፣ አድዋ፣ ፋሲል የሚለውን እንኳ ትተን በቅርቡ የታወቁ የኛን አስገራሚ ታሪኮች እንመልከት።
በመካከለኛው ክ/ዘመን ወደ አረብ ሀገር፣ ወደ ኤሺያም እስከ ህንድ በባርነት የሚላኩ ብዙ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ጥቁሮችም ነበሩ። ታዲያ በዚህ አንገት የሚያስደፋ ታሪክ ውስጥ የሚገርም የኢትዮጵያውያን ታሪክ አለ።
ህንድ ተሽጠው የነገስታቱ አገልጋዮች የሆኑ ኢትዮጵያውያን መፈንቅለ መንግስት አድርገው ለአጭር ጊዜ የቆየ ዳይናስቲ መስርተው ነበር። እናም ከፊል ህንድን፣ ኔፓልን እና ባንግላዴሽን ለተወሰነ ጊዜ ገዝተው ነበር።
በተመሳሳይ ህንድ ውስጥ የነበረ ሌላ ኢትዮጵያዊ ባርያ ከባርነቱ ወጥቶ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ለብዙ ዘመናት መርቷል።
ማሊክ አምባር የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ በ15ኛው ክፍለ ዘመን የመራ።
1. ሌሎች እርዳታ ካላደረጉልን አንችልም
2. ያለ ሌሎች እርዳታ እንችላለን፣ ነገር ግን ሙከራችን እንዳይሳካ የሚያሰናክሉን አሉ።
መላምቶቹን ከመመልከታችን በፊት እስኪ ይህንን ጥያቄ መልሱ፦ ሁለተኛው መላምት የማያሳምን ምክንያት መደርደር ይመስላል?
ለማንኛውም የመጀመሪያውን መላምት እንመልከት። በርግጥም እስካሁን በተከታታይ የውጪ እገዛ ተደርጎልናል። ራሳችንን ችለን እድገትን ወይም ቴክኖሎጂን የሞከርንበት ጊዜ የለም። አፄ ቴዎድሮስ እንኳ የኢንግሊዝ ባለሙያዎችን ተጠቅሞ ነው መድፎቹን ያሰራው። እሱ ህልሙ ኢትዮጵያውያን ከፈረንጅ ተምረው፣ ከዛ በኋላ ግን በራሳቸው መስራት እንዲችሉ ለማድረግ ነበር። ኢንግሊዞችም ያንን እምቢ ስላሉ፤ ውጤቱ ምን ሊሆን ይችል ነበር የሚለውን ለምናብ የምንተወው ይኾናል።
ነገር ግን የቴዎድሮስን ሙከራ የሚመስል ሌላም ሙከራ ነበር። በ20ኛው ክ/ዘመን የመጀመሪያዎቹ አሰርት ዓመታት ውስጥ አንድ እንቅስቃሴ ነበር። ይኸውም ከወደ ኤሺያ የተሰማው የጃፓን እድገት የፈጠረው መነሳሳት ነበር። ታዲያ እነዚህ ሰዎች በጃፓን እንዲማረኩ ያደረጋቸው፣ ጃፓኖች ባህላቸውንና የንጉሳዊ ስርአታቸውን ሳይተዉ ቴክኖሎጂንና ኢንዲስትሪን ወደ ሀገራቸው ማስገባት በዚያም ማበልጸግ መቻላቸው ነበር።
ምንጭ
በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን የነበሩ የተማሩ ወጣቶችም ስለ ጃፓን እድገት ከማሰብ አልፈው፣ ያንን ለውጥ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣትም መሬት የረገጠ ስራ መስራት ጀምረው ነበር።
የጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ኅሩይ ወልደ-ሥላሴም ከባልደረቦቹ ጋር ጃፓን ድረስ አቅንቶ ከጃፓኖች ጋር ግንኙነት ጀምሮ ነበር።
ታዲያ ይህን እንቅስቃሴ የሚያቋርጥ ክስተት ተፈጠረ። ጣልያንን ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ ወረረች፣ ንጉሱም ከሀገር በመሸሹ ሀገሪቱ ብልጽግናን ትታ ለህልውናዋ የምታጣጥር ሆነች። አርበኞችም በመላው ሀገሪቱ በሽምቅ ውጊያ ተሳትፈው ከወራሪው ኃይል ጋር መዋጋት ጀመሩ፣ ነገሩም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መቋጨት ጋር አብሮ ሲቋጭ፣ ከጃፓን ጋር የማደጉም ነገር ተረሳ፣ ጃፓንም በጦርነቱ ደቃ፣ የአሜሪካ ፍጹም ተገዢና ባርያ ስለሆነች ያ በዚያው ቀረ።
ታዲያ ጣልያን በጊዜው ኢትዮጵያን ያጠቃችበት አንዱ ምክንያት ያንን የኢትዮጵያ እና ጃፓን ግንኙነት ለማቋረጥ፣ ኢትዮጵያም ለእድገት የምታደርገውን ጥረት ለማጨናገፍ አስባ እንደሆነ ይነገራል። ይህም በታሪክ የታወቀ እውነታ እንጂ መላምት ወይም የግል ሀሳብ አይደለም።
ይህ ታዲያ ቅድም ካነሳናቸው መላምቶች ወደ ሁለተኛው መላምት ይመራናል። ምናልባትም እኛ እንዳናድግ ይፈለግ ይሆን?
ይህ እንዲሆን ምን ምክንያት ይኖራል? እስኪ እናስበው።
ጂኦ-ፖለቲካን እንመልከት። ያለንበት አከባቢ የህንድ ውቂያኖስ እና ቀይ ባህር መጋጠሚያ አከባቢ ላይ ነው። የዓለም 70% ንግድ የሚተላለፍበት እጅግ ወሳኝ ቀጠና። በመላው ታሪካችን ከሶማሊላንድ እስከ ኤርትራ ያለውን የባህር ዳርቻ ወይ ተቆጣጥረናል፣ አልያም ተመኝተናል። በኛ እጅ ቢገባ ደግሞ ምን ይፈጠራል? አከባቢውን አንድ የሚያደርግ ኃያል ሀገር ብንሆንስ?
ያ የሆነ ለት፣ እንደ ቱርክ እና ኢራን የጂኦ-ፖለቲክስ ከባድ ሚዛን ያለን ሀገር እንሆናለን። ቱርክ የአውሮፓ፣ መካከኛው ምስራቅ፣ ማዕከላዊ ኤሺያ (ካውካሰስ) እና ሜዲትራኒያን መገናኛ ማዕከል የሆነ ስፍራ ላይ ያለች ሀገር ነች። በዚያ በመኖሯ ብቻ ማንም በቀላሉ ሊያጠፋት የማይችል፣ አሜሪካንና ሩሲያን የምትገዳደር ሀገር ሆናለች። ኢራንም የኤሺያ ኮሪደር ላይ የተቀመጠች፣ የዓለም ከፍተኛው ነዳጅ የሚመረትበት የፋርስ ባህረ ሰላጤ ጎን ያለች ሀገር ነች። ስለዚህ አሜሪካም ጭምር በቀላሉ የማትደፍራት በሁሉም የተከበረች ሀገር ሆናለች። ቱርክ እና ኢራን በዚያ ወሳኝ ስፍራ ላይ መገኘታቸው ብቻ አይደለም፣ በዚያ የተፈጠሩ ሃያል ሀገር መሆናቸው ጭምር ነው።
ኢራን ኢሺያን እና አውሮፓን የሚያገናኙ ረጅም የባቡር መስመሮችን በውስጧ የምታሳልፍ ወሳኝ ሃገር ነች።
እኛም ባለንበት የቀይባህር-ህንድ-ውቂያኖስ ስፍራ ላይ ኃያል ሀገር ከሆንን በኋላ የሚያስቆመን አይኖርም። ስለዚህ የዓለም ሃያላን አማራጫቸው ምንድን ነው? መጀመሪያውኑ ሃያል ሀገር እንዳንፈጠር ማድረግ ነው። ባህሩን መንሳት ነው። ጅቡቲ፣ ኤርትራ የሚባሉ አርቴፊሻል ሀገራት ፈጥረው እኛን መዝጋት ነው።
እሺ ይህ አሳማኝ ይመስላል፣ ግን በምን መረጃ ወይም ማስረጃ እንደግፈው? አንደኛ በተጨባጭ ከምናየው ሁኔታዎች ያንን እንደ ማስረጃ (circumstantial evidence) ማቅረብ እንችላለን። ሁለተኛ ደግሞ ራሳቸው ያሉትን ማቅረብም እንችላለን። ምን አሉ? ለሚለው፣ ሮማን ፕሮሻዝካ የተባለ ኢንግሊዛዊ፣ "Abyssinia the power barrel" በሚለው መጽሐፍ ኢትዮጵያ ማለት ልትፈነዳ ትንሽ ምክንያት የምትፈልግ የባሩድ በርሜል ናት ብሎ የጻፈውን መመልከት ነው።
"ጠያይሞቹ ኢትዮጵያውያን እንደ ሌላው ጥቁር አፍሪካዊ እኛ ነጮችን አይፈሩንም፣ በነሱ ሀገር ታላቅ መንግስት ከተፈጠረ ማናችም ማስቆም የማንችለው ሃይል በምድር ላይ ይነሳል፣ ስለዚህ መንግስታቸውን በሂደት እናድክም፣ ጠንካራ መንግስትም እንዳይፈጠር እንስራ መላው ዓለም ይተባበረን"
እነዚህ በመጽሐፉ ላይ ከተከተቡት ቃላት ጥቂቶቹ ናቸው። ስለዚህ የውጪ አካላት እኛን ለማዳከም ምክንያት አላቸው ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍም ጽፈውታል። ይህንን መረጃ የሚደግፈው ደግሞ የአረብ ሀገራት ብዙ "ነፃ አውጪ" ቡድኖችን (ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ህወሓት) ፈንድ አድርገው እና አሰልጥነው የላኩበንና ሊገነጣጥሉን የሞሩበት፣ በከፊልም የተሳካላቸው ክስተት ነው። ሻዕቢያ የምጽዋ ወደብን ከወሰደ በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይልን ሙሉ በሙሉ ለማውደም የሄደበት ርቀት ይህንን ቁልጭ አድርግ ያሳየናል።
ታዲያ የውጪ አካላት ተጽዕኖ ከፈጠሩብን እኛስ ያንን ተቋቁመን ለመውጣት ምን ከበደን?
ይህም ሌላ ጥያቄ ነው። በአንድ በኩል፣ ከላይ የተነሳው እኛን የመገነጣጠልና በዘር ፖለቲካም የማባላት ጥረት ተሳክቷል። እንዴት እንደግ እንዴት ከድህነት እንውጣ የሚለውን ትተን በጥላቻና በዘረኝነት መጠላለፍን መገዳደልን ተያይዘን ጊዜአችንን ገድለናል። እየገደልንም ነው። ጊዜአችንን ብቻ ሳይሆን ወንድማችንንም ገለናል፣ እየገደልን ነው።
ከዛም በላይ ግን የሀገራችን የፖለቲካ መዋቅር የተሰራበት አሰራርም እኛን ለማዳከም ታስቦ ለአሰርት ዓመታት የተሰራ ነው። ከ60ዎቹ ትውልድ ጀምሮ በአሜሪካውያንና በኢንግሊዞች የተዘረጋው የደህንነት መረብ፣ ያ መዋቅር ስር እንዲሰድና ጠንክሮ እንዲቆም አድርጎታል። በተለይ ከደርግ በኋላ ባለው ጊዜም የባሰ ሆኗል። አብዛኛው ከፍተኛ የስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች በእውቀታቸውና በችሎታቸው ሳይሆን በአጋጣሚዎች እና ለመዋቅሩ ባላቸው ታማኝነት ቦታውን ያገኙ ናቸው። ጥቂት የተማሩ እውቀት ያላቸው ሰዎች ቢኖሩም፣ የመንግስት መዋቅር እንዳይሞትና ስራውን እንዲሰራ ከማድረግ ያለፈ ተጽዕኖ መፍጠር አይችሉም።
ያለው ስርአት ወጣቶች ተምረው ሰርተው እንዳይለወጡ፣ በተለይ ቴክኖሎጂ ነክ ነገሮች ላይ ሀገር የሚለውጥ ስራ መስራት እንዳይችሉ የሚገድብ፣ ቀፍድዶ የሚያስር፣ ተስፋም የሚያስቆርጥ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠር የኢንጂነሪንግ ምሩቅ ስራ አጥቶ ቤተሰቦቹ ጋር የሚኖረው ለሱ ስራ የሚሰጥ፣ የሱን እውቀት የሚጠቀም ስርአት እንዳይኖር ለአሰርት ዓመታት ስለተሰራ ነው። ምክንያቱም ለእሱ እድል የተሰጠው ቀን፣ ከጋምቤላ እስከ ሶማሊላንድ፣ ከቦረና እስከ አሰብና ምጽዋ ያለውን አከባቢ የሚለውጥ፣ የሚያንቀሳቅስ ተግባር መስራት ይጀምራል። ግዙፍ ኢኮኖሚ፣ ትልቅ ሀብት፣ ትልቅም የፖለቲካ ሃይል መገንባት ይጀምራል።
ከላይ ያልነው መረብ ደግሞ exactly ይህ እንዳይፈጠር የተቀመጠ ነው። መዋቅሩ ይህንን ለማፈን፣ ለመኮርኮም የተፈጠረ ነው። እንደነ ኤርሚያስ አመልጋ ያሉ ሰዎች አዳዲስ ሀሳብ አምጥተው ቢዝነስ በጀመሩ ቁጥር እየተኮረኮሙ ፋብሪካቸውን ዘግተው ከሀገር የወጡት በዚሁ ምክንያት ነው።
ስለዚህም፣ ከውጪ ጫና አለብን የሚለው እውነት ነው። ከባድ መዋቅር እንደ መርግ ተጭኖናል የሚለውም እውነት ነው።
ይህን ሁሉ ካልን በኋላ ግን ሀሳቡን ሁሉ የሚያስረው አንድ መልስ አለ። ኢትዮጵያ ለምን በቴክኖሎጂ አልበለጸገችም ስንል
እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው።
በምድር ላይ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሚሆን አንዳች ነገር የለም። አንድ ነገር ካልተፈጠረም እግዚአብሔር አልፈቀደም ማለት ነው።
ለዚህ ነው አስር ሃያ ምክንያቶች ተደርድረው የመጨረሻ ድምር ውጤቱ አለማደጋችን የሆነው። ይህንን እድገታችንን እግዚአብሔር በሆነ ምክንያት አልወደደውም።
ምናልባት ያ ምክንያት ቢቀር ወይም ቢቀረፍ ይፈቅድልናል።
አሁን ነገሮች ባሉበት ሁኔታ ግን አልፈቀደም። ስለዚህ ለም አፈራችንንና ቤተክርስቲያናችንን ይዘን፣ የጭቃ እና የቆርቆሮ ቤታችን ውስጥ ሆነን የእርሱን ፈቃድ እንጠባበቃለን። ካልደረስንበትም አያቶቻችን እሱን እያመሰገኑት እንደኖሩት እኛም ምስጋናው ምግብ ሆኖን እሱን ይዘን እንሞታለን።

ከባርነት ውጪም ኢትዮጵያውያን የመንን ለብዙ ዘመናት ገዝተዋል።
አድዋንም ብንመለከት መላውን ዓለም ያስደመመ፣ ጥቁሮች ይችላሉ የሚለውን መልእክት ያስተላለፈ ክስተት ነበር። ያንንም ያደረግነው እኛ ነን። ከዚያም ቴክኖሎጂን ወደ ሀገራችን አስመጥተን ዘመናዊነትን አምጥተናል። ግን በሚፈለገው ደረጃ አልሆነም እንጂ።
ስለዚህ አስቀድመን ላነሳነው ጥያቄ፣ "እኛ ጥቁር ስለሆንን አንችልም" የሚለው መልስ ትክክል አይደለም ማለት ነው። እንችላለን።
ከቻልን ታዲያ ለምን እስካሁን ኋላ ቀር ሆንን?
አልፈለግንም ይሆን? እንዳንል ፈልገናል። ነገስታቱ ዘመናዊነትን እና ስልጣኔን ሊያመጡልን ለፍተዋል፣ በከፊልም ተሳክቶላቸዋል፤ ህዝቡም በሂደት ተቀብሎታል።
ስለዚህ ለምን በቂ በሆነ ደረጃ አልቻልንም? ለዚህ ደግሞ ሁለት መላምቶችን ማቅረብ እንችላለን፦

Blogger Comment
Facebook Comment