ዘመናዊው የትምህርት ስረአት ካሉበት ችግሮች ውስጥ አንዱ ደግሞ የሚወስደው ጊዜ እና የሚጀምርበት፣ የሚያበቃበትም ሁኔታ ነው። ይህንን ስረአት የመሰረቱት ሰዎች ምን እየሰሩ እንዳሉ በደምብ ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች መሆን አለባቸው።
አንዱ የዘመናዊው ትምህርት ስረአት መገለጫ በእድሜ የመከፋፈሉ ሂደት ነው። በዚህም ትምህርት በዓመት በዓመት ተከፋፍሎ፣ ለትማሪዎች የሚሰጠውም ተቀንሶ ተቀንሶ በየዓመቱ መሆኑ ነው። እናም በዚህኛው ዓመት ይህን ያህል ትምህርት፣ በቀጣይም ይህን ያህል በቀጣዩም ይህን ያህል እየተባለ ይቀጥላል።
ይህም ከእውቀት አሰጣጡ አንጻር ካየነው የተለያዩ ጉዳቶች አሉት። አንደኛ እውቀቱን ሽተው እጅግ ደስ ብሏቸው የሚማሩ ይኖራሉ። እነሱም አሁን ያገኙት እውቀት ደስ ብሏቸው ወደ ቀጣዩ በቶሎ ማለፍ ይፈልጉ ይሆናል። ነገር ግን ሰረአቱ ስለማይፈቅድ ቀስ ብለው እንዲሄዱ ያደርጋል። በርግጥ ጥቁት "ብሩህ አእምሮ ያላቸው" ተማሪዎች ይህንን እድል አግኝተው ትምህርታቸውን በትንሽ እድሜያቸው የሚጨርሱ ይኖራሉ። ነገር ግን ብዙዎቹ ያንን እድል አያገኙም። አንድ ሰው ትምህርቱ ከተመቸው እና በፍጥነት መቀበል ከቻለ፣ ቶሎ ጨርሶ ወደቀጣዩ እውቀት ማለፍ፣ አልያም ደግሞ ህይወቱን መቀጠል መቻል ይኖርበታል። ነገር ግን ዘመናዊ ትምህርት ሰዎችን እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል። አብዛኛው ሰው 18፣ 19፣ እስኪሆነው እንዲጠብቅ ይገደዳል። ይህም የራሱ ትልቅ ችግር አለው። ወደ ኋላ እንመለስበታለን።
ሌላው ደግሞ ትምህርትን በዚህ ሁኔታ ቀስ ብሎ የመስጠት ሁኔታ፣ ሰዎችን አእምሮአቸው የቀለም እና ምሁራዊ (የተሻለ ቃል ከማጣት ነውን፣ የኢንግሊዘኛውን "intellectual" የሚለውን ያዙት) እድገታቸው እንዲያዘግም እና የሆነ ቦታ ላይ እንዲገታ ያደርጋል። በዚህም ምክንያት በተወሰነ ደረጃ ብቻ ማሰብ የሚችሉ፣ ከበድ ያሉ ሃሳቦችን ማሰላሰልና መፈላሰፍ የሚከብዳቸው ተማሪዎችን ያመርታል። ይህም እጅግ ታስቦበት ነው። እንደነ ሮኪፌለር ያሉ ቤተሰቦች ዘመናዊ የትምህርት ስረአትን ሲያስጀምሩ ለነሱ ድርጅቶች ጥሩ ሰራተኛ የሚሆኑ ዜጎችን እንጂ ራሳቸውን ችለው ማሰብ የሚችሉ ዜጎችን እንዳይፈጠሩ ለማድረግ አስበው ነበር። ምክንያቱም እንደዚያ ማሰብ የቻለ ሰው መጠየቅ ይጀምራል። እኔ በትንሽ ደሞዜ ግብር እየተቆረጠብኝ ቢሊየነሮች ለምን ግብር አይከፍሉም ብሎ ይጠይቃል፣ ቢሊያነሮች ከባዶ መሬት ገንዘብ አትመው የኔን ቤት እና መኪና የመግዛት አቅም ለምን ያዳክማሉ ብሎ ይጠይቃል። ለነሱ ባርያ የምሆን ከሆነ ለምን ለነሱ እሰራለሁ፣ የደሞዛቸው ጥገኛ ለምን እሆናለሁ ብሎ መጠየቅ ይጀምራል።
ስለዚህ ምን ያደርጋሉ፣ ያንን የመጠየቅ ችሎታ መግደል። ሰዎች በሽምደዳ ብቻ ላይ እንዲያተኩሩ፣ የሚማሩት ነገር ከየት እንደመጣ እንዴት እንደመጣ እንዳይጠይቁ፣ በውስጡ ስህተት ካዩ ለምን ያ ሆነ ብለው አእምሮአቸውን እንዳያሰሩ ማድረግ ነው። እነዚህ ነገሮች በተለምዶ አእምሮን በከባዱ ማሰራት ይጠይቃሉ። የተወሳሰቡ የሃሳብ ሰንሰለት መረዳት የመቻል እና እጅግ ትልቅ አርቆ አሳቢነት፣ የአእምሮን ጡንቻ በደምብ ማሰራትን የሚጠይቁ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ በትምህርት ተቋማቱ ሰዎች ይህንን ማድረግ እንዳይችሉ በዘዴ መገደብ ይካሄዳል። ሳይንሱ ቲዮሪው እንዲህ ብሏል፣ ኒውተን ወይም ሜንደል ወይም ሽሮዲንገር እንዲህ ብሏል፣ እሱ ስላለ መቀበል ነው ያለብን፣ እንጂ የሱን ሃሳብ ሰርስረን ገበተን ስህተቱን ማውጣት እና ትክክል ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መመርመር የለብንም የሚለውን አስተሳሰብ ያመጣል።
ያ ብቻ አይደለም። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በየዓመቱ የሚሰጠው ትምህርት፣ አንዳንዱ ተደጋጋሚነት ስላለው፣ በዘዴ የአእምሮ አጠባ ለማካሄድም ይጠቅማል። በየዐመቱ ለ 12 ዓመታት ምድር ድቡልቡል ኳስ ናት፣ ጸሃይ ሰማይ ላይ ስትሄድ ብታያትም አትሄድም ምድር ናት የምትዞራት፣ የመጣከው ከዝንጀሮ ነው። እንዲህ እየተባለ ሰው ተደጋግሞ ሲነገረው የሆነ ጊዜ ላይ ነገሩን እንደ እውነታ ነው የሚቆጥረው። ከዚያን ያንን የሚቃወም ሰው ሲያገኝም እንደ አላዋቂ፣ ጅል፣ ወይም መሃይም ነው የሚቆጥረው። ለሱ ያ ሰው "ወተት ነጭ አይደለም፣ እሁድ ሰንበት አይደለም፣ አካፋ አካፋ አይደለም" እንደሚል አድርጎ ነው የሚታየው። ያንን ችግር ነው የሚያመጣው።
ቀደም የተውነውን ሃሳብ መልሰን ካነሳነው ደግሞ የትምህርት ስረአቱ ሰዎች እስከ 18 19 ዓመታቸው እንዲቆዩ ያስገድዳቸዋል። በሆነ፣ ማን እንዳመጣው፣ ከየት እንደተገኘ በማናውቀው ምክንያት፣ 18 ዓመት ማለት ሰው ድንገት አዋቂ የሚሆንበት እድሜ ነው ተብሎ ተነግሮናል። ሰዎች ራሳቸውን ለመቻል፣ ስራ ለመስራት፣ መኪና ለመንዳት፣ ወሲብ ለማድረግ የግድ እዚያ ላይ መድረስ አለባቸው ተብሏል። እናም ያ ምክንያት ተደርጎ እስከዚያ እድሚያቸው ድረስ ሰዎች እንደ ህጻን እንዲታዩ ይደረጋሉ። ያም ድንገት የአእምሮና በተለይ የብስለት ሂደታቸውን እጅግ እጅግ ያዘግመዋል።
ወንዱም ተንቀሳቅሶ ነገሮችን የሚለማመድበት እድሜ፣ ሴቶችም ወደ ትዳር የሚደርሱብት እድሜ ነበር ያ ድሮ ላይ። ከዚያ ትምህርት ሲመጣ፣ ስልጣኔም የሚመጣው ከትምህርት ነው የሚለው ሃሳብ በሆነ ምክንያት በሁሉም ሰው አእምሮ ላይ ስለተቀረጸ፣ ሰዎች በህይወታችው ወሳኝ ነገር የሚያደርጉብትን እድሜ በዚያ ያባክናሉ። በአስራዎቹ መጨረሻ ወጣቶች ብዙ ነገር ማደረግ እና መማር የሚችሉበት እድሜ፣ በትምህርት ተቋማት ይባክናል። ወጥተው ሙያን ሊማሩበት የሚችሉበት እድሜ ማለት ነው።
ወጣቶች በ16 17 18 ዓመታቸው ብዙ ማሰብ፣ ብዙ ማንበብ፣ ብዙ መጻፍ፣ ብዙ መፈላሰው የሚጀምሩበት እድሜያቸው ነው። እስኪ ራሳችሁን ሁሉ አስቡ። በዚያ እድሚያችሁ ያነበባችኋቸው መጻህፍት፣ ከጓደኞቻችሁ ጋ የተወያያችኋቸው ነገሮች፣ በአእምሮአችሁ ያሰላሰላችሁት ነገሮች እስኪ ወደ ኋላ ተመልሳቸው አስቡ። "በእውነት እኔ ነበርኩ ግን ያን ሁሉ ያደረግሁት?" ማለታቸው አይቀርም። ያንን ጊዜ ነው፣ ለህይወታቸሁ ወሳኝ ነገር ልታደርጉባቸው የምትችሉብትን የምታባክኑት። ለዚህ አሪፍ ምሳሌ እናንሳ። ብዙ ወጣቶች በኛ ሃገር ጭምር በ 16 17 ዓመታቸው ኮምፒውተር ላይ ፕሮግራም አድርገው ሶፍትዌር መስራት ይጀምራሉ። በዚያ እድሚያቸው እጅግ የሚያስደንቁ ነገሮችን ይሰራሉ። ግን ያንን የሚያበረታታ ነገር ስለሌለ፣ ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ይባሉና፣ 5 ዓመት ያባክናሉ። ብዙ ጊዜ ግን እነዚያ ልጆች ከዩኒቨርሲት የሚያገኙት እውቀት እምብዛም ነው፣ እነሱ ቀድመው የሚያውቋቸው ነገሮችን ነው በብዛት ደግመው የሚማሩት። አዲስ ነገር አይማሩም ማለት አይደለም፣ ግን ያንን ነገር በ 21 እና በ 22 ዓመታቸው የተማሩትን ነገር በ17 ቢማሩትም እኩል ይረዱት ነበር።
ግን እስከ 22 እንዲጠብቁ በመደረጉ ከእድሚያቸው ላይ ወሳኝ ዓመታትን ትነጥቀዋል ብቻ ሳይሆን ባክኖባቸዋል። የሚጠቅማቸውን እና እነሱ ለመረጡት መስክ የሚሆነው ነገር ሳይሆን ከዚህም ከዚያም ተሰብስቦ ሁሉንም እንዲማሩ፣ አንዳንዴም የማይጠቅማቸውን አሰስ ገሰስ ይዘው አእምሮአቸውን እንዲሞሉ እየተደረግ እድሚያቸው ይባክናል።
ይህም የባከነ እድሜ እና በተገቢው ልክ እንዳይበለጽግ የተደረግ አእምሮ፣ የስረአቱ ገንቢዎች እንደፈለጉት የሚገዙት ታዛዥ፣ ለገበያው፣ ለካፒታሊስት ስረአቱ ተገዢ፣ ከተቀመጠለት መስመር የማይወጣ፣ የሚፈራ ደካማ ሰውን ለመፍጠር ይረዳል።
ይቀጥላል።

Blogger Comment
Facebook Comment