ኢትዮጵያ ውስጥ ከአዕምሮ በላይ የሆነ የስነልቦና ጦርነት እየተካሄደ ነው


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ሐኪሞች ጤናን በሚያቃውስበት፣ የሕግ ሰዎች ፍትሕን በሚከለክሉበት፣ መካነ አዕምሮዎች ዕውቀትን በሚያበላሹበት፣ መንግስት ነፃነትን በሚያፍንበት፣ መገናኛ ብዙኅን መረጃን በሚያጠፋበት፣ ሃይማኖት ሞራልን በሚያበላሽበት፣ ባንኮች ቁጠባን ​​በሚገድሉበት ሀገር ውስጥ ነው የምንኖረው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከአዕምሮ በላይ የሆነ የስነልቦና ጦርነት እየተካሄደ ነው።

ከማናችንም የማሰብ፣ የማስተዋል፣ የብልጠት አቅም በላይ የሆነ፤ ብዙ ዓመታትን የፈጀ ቲያትር ተደርሶ እየተተገበረ ነው።

መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን እጅግ ፈታኝ፣ እጅግ ከባድ፣ እጅግ አስቸጋሪ፣ እጅግም አድካሚ ነው የሚሆነው። እግዚአብሔር ይርዳን።

በጥንቷ ሱሜሪያ በአሁኗ ኢራቅ ውስጥ አኑናኪ ተብለው የሚታወቁ አማልክቶች ነበሯቸው። እነዚህም ከሰማይ የወረዱ ግዙፋን ሰው መሰል ፍጥረቶች እንደነበሩ ይታመን ነበር። 

እነዚህ አኑናኪዎች ታዲያ አፈጣጠራቸው ሁሉ ነገራቸው ረዓይት/ኔፍሊሞችን ይመስላል። አንዳንዶቹ የዓሳና "reptile" መሰል አካል አላቸው። አፈ ታሪካቸው እንደሚያስቀምጠው ለሰው ልጆች እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጭካኔ ነበራቸው። በጭካኔ ነበር የሰው ልጆችን የሚገዟቸው። እንዲሁም ከሰው ልጆች በላይ የረቀቀ ከፍተኛ እውቀት ነበራቸው።

ምናልባትም ዛሬ ላይ ዓለምን የሚገዙት የጭለማው ዓለም ገዢዎችም የነዛው የሬፕታይሎቹ የዘር ሐረጎች ሳይሆኑ አይቀሩም። እነዚህኞቹ ዓለምን የመግዛት መርሃቸው ከፍተኛ ጭካኔ ሲሆን ለሰው ልጆች ከፍተኛ ጥላቻ እና ንቀት ያላቸው ናቸው። ሰዎችን በሙሉ ነጭ ጥቁር ኤሺያዊ ሳይቀር እንስሳ፣ መንጋ አድርገው የሚያስቡ ናቸው።

እናም፣ ምናልባት የተለያዩ የሚስጥር ማህበራት ጀርባ ሆነው ዓለምን የሚገዙት እነሱ ሳይሆኑ አይቀሩም።

የዓለም ፖለቲካ ፍጹም ቲያትር መሆኑ የታወቀ ነው። የዓለም መሪዎች በሙሉ ተመርጠው የተቀመጡ ተዋንያን ናቸው። ፑቲን በሉት፣ ትራምፕ በሉት፣ ዘሌንስኪ በሉት፣ግራኝ ዐቢይ አሕመድ በሉት፣ ሺ ዢምፒንግ በሉት ሁሉም ትልቁን ድርሰት የሚተውኑ ተዋንያን ናቸው። እያንዳንዱ የሚፈጸመው የሀገራት መስማማትና መጣላት፣ መዋጋትና መተባበር በሙሉ ቀድሞ የታቀደ ድርሰት ነው።

የጭለማው ሰራተኞች ይህንን ሁሉ ከጀርባ የሚቆጣጠሩበት እጅግ የተራቀቁ የስለላ መረቦች በመላው ዓለም አላቸው። በኛም ሀገር በተመሳሳይ ያ መረብ አለ።

በኛም ሀገር፣ የየራሳቸው ኔትወርክ ያላቸው፣ ከዋናው ኔትወርክ ተመርጠው የመጡ፣ በአገዛዙም በተቃዋሚውም ውስጥ ያሉ አካላት አሉ። ፍጹም የማይተዋወቁ መስለው የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ። እነሱ የተጣሉ መስለው ህዝብን የሚያጫርሱ፣ ደም የሚያቃቡ፣ የሚጠርጉ ናቸው።

ይህ ሁሉ ሲፈጠር ፈጣሪ ምን ይላል? መልሱ ቀላል ነው። የኛ ኃጢአት ሲበዛ ፈጣሪ እነዚህን አካላት እየተጠቀመ ይቀጣናል። እነሱን እንደ መሳርያ ይጠቀማል። ሳያውቁት ብልሃት ያላቸው መስሏቸው የሱን ፈቃድ ይፈጽማሉ። ያለርሱ ፈቃድ ግን አንዲትም ነገር ማድረግ አይችሉም። የሰውን አንዲት ፀጉር እንኳ መንካት አይችሉም።

እነዚህ አካላት የሌሉበት ቦታ የለም። የመንግስት መገናኛብዙኅን፣ የተቃዋሚ መገናኛብዙኅን፣ ሙዚቀኞች፣ ሌሎችም ፋኖ፣ ሸኔ ወዘተ የሌሉበት የለም። እንደውም በቅርቡ ፋኖ ውስጥ ሰርገው ገብተው ትግሉን በራሳቸው መንገድ ሲቀርጹት ልታዩ ትችላላችሁ። በዚህም እርስ በርሱ ሊያጫርሱት ይችላሉ። ከፍተኛ እልቂት በዚህ ምክንያት ሊመጣ ይችላል። መንግስት ባለበት ሀገር የራሳቸው የስለላ ኔትወርክ የፈጠሩ ሰዎች ከጀርባው እንዳሉ መጠራጠር የለባችሁም።

ብቻ ስለዚህ ነገር ከዚህ በኋላ ብዙ አልልም። የሚሆነውን እናያለን።

እኛ ግን ንስሐ እንግባ። ወደ ፈጣሪያችን እንመለስ። ትዕዛዙን እንጠብቅ። ወንዱ ፀጉር ከማንጨብረርና ከቁማር፣ ሴቷ ሱሪ ከመልበስ እንታቀብ። በተረፈ በጸሎት እንትጋ። መጪው ጊዜ እጅግ ከባድ ነውና እግዚአብሔር ያጥናን። ጠራጊዎቹ ጠርገው ሲጨርሱ ራሳቸውም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ያልፋሉና እኛ ግን በጾም በጸሎት በንስሃ ሆነን የእግዚአብሔርን ፍርዱን እንጠብቅ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment