✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የሚመጣውን የእሳት ፍርድ እስካሁን አላየህም
❖ የጽዮን ቀለማት ❖
'አውሮራ ቦሪያሊስ'፣ እንዲሁም 'ሰሜናዊ ብርሃናት' በመባል የሚታወቀው፣ በፀሐይ ላይ ባለው ማዕበል የሚጀምሩት ተከታታይ ግንኙነቶች ናቸው። “በአስራ አንድ አመት ዑደት ውስጥ የሚጨምሩት እነዚህ የፀሐይ አውሎ ነፋሶች የተሞሉ ቅንጣቶችን ወደ ፀሐይ ይለቃሉ” ይባላል። በስተ ደቡብም ይህ ክስተት በአውስትራሊያ ሰማያት ላይ በመታየት ላይ ናቸው። አሁን ምልክት እየተሰጠው ያለው የአንግሎ-ሳክሰኑ ዓለም መሆኑን ልብ እንበል።
በኢትዮጵያ ዙሪያም ዓረቢያን እና ጭፍሮቿን የሚቀቅላቸው የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ሰዶም እና ገሞራ ካሊፎርኒያ እና ዓረቢያ ወዮላቸው!
❖[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፲፪፥፲፯]❖
“ባይሰሙኝ ግን ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ አጠፋውማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
😇 እግዚአብሔር የዚህ ማዕከል ነው። እግዚአብሔር የሚያደርገው ይህንኑ ነው። እግዚአብሔር ስለዚህ ዘመን በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ተናግሯል። በነቢያቱ በኩል፣ ለዚች ዓለም አስፈሪ የሆነ የእሳት ፍርድ እንደሚመጣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለሰው ልጆች ተናግሯል። እና አሁን፣ እነሆ፣ በእኛ ላይ በመፈጸም ላይ ይገኛል። በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠሩትን ንጹሐንን እንደ ዝንብ ገድሎ፣ የእግዚአብሔርን ተፈጥሯዊ ሕግጋትን ጥሶና ሥራውንም ተፈታትኖ ከእሳት ፍርድ የሚያመልጥ መንግስት፣ ግለሰብ እና ማህበረሰብ በጭራሽ ሊኖር አይችልም።
❖[የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፬]❖
፩ ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ። ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።
፪ ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
፫ ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።
፬ በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
፭ ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፥ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
፮ በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
❖[መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፲፬-፲፭]❖
Blogger Comment
Facebook Comment