መልዕክት ለኦሮሞ ምድር ህዝብ




 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ከቃሉ አንዲቷም ፈፅሞ በማትታበል በአንድ አምላክ ስም
አምላክ ሁሉን ህዝብ ሲያይ በእኩል አይን ነው። ራሳችንን በወገንተኝነት፣ በጎጥ፣ በሀብት፣ በምን በምን ብንከፋፍል እዚሁ ለኛው ይሆናል እንጂ፣ የእግዚአብሄርን አይን ልንጋርደው ወይም ተፅእኖ ልናሳድርበት ፈፅሞ አይቻለንም።

በሚመጣው ሁሉ በእግዚአብሄር ፍርድ የሚቀሰፈውም ሆነ የሚድነው እያንዳንዱ ግለሰብ የሚመዘነው ዘመን በማይለውጠው በነበረው በሚኖረው አምላካዊ ሚዛኑ ነው እንጂ የኛ የቡድን ወይ የዘር መለያ ወይ ጎራ በሱ አይን ፊት እንደሌለ ነው የሚሆነው። አንዴ በሱ ፊት ተመዝነን ከወደቅንና ለቅጣት ከተወሰነብን ምን አለም ቢሰለፍ፣ ምን ተአምር ቢሰራ የሚያድነን ከቶ ሊኖር አይችልም፤ ደግሞ በዛው መጠን በሱ ፊት አንዴ ተመዝነን ከተመረጥን ምን እሳት ቢዘንብ፣ የእልቂት መአበል መሀል ብንገባ ከቶ የሚነካን ሊኖር አይችልም።


እውነተኛው ኦሮሞ አባቶችህ ማንነት በየዋህነት፣ ሰው ወዳድነት እንዲሁም ቸርነት የሚታወቅ ሆኖ ሳለ፣ አይደለም ለሰው ከተፈጥሮ ጋር እንኳን ተስማምቶ ተዋህዶ የሚኖር የብልህ ህዝብና ባህል ማንነት ያላቸው ሲሆኑ፣ ይህም ዛሬም ድረስ በገጠሩ ጠልቀው ሲገቡ በግልፅ የሚታይ እውነተኛው የኦሮምያ ክልል ህዝብ ማንነት ሆኖ ሳለ፣ ዛሬ ፈፅሞ መጤና ክፉ በሆነ ጨርሶም ማንነትህና ያባቶችህ ባህልና ስነልቦናም የሚጠየፈውን አፀያፊ ሀሳብና ተግባር አይን ያወጣ ገፊነት፣ ራስወዳድነት እንዲሁም ጥላቻን አንግበው በፍፁም አዲስ ማንነት በስምህ ይዘው ካንተ የወጡ በመሆናቸውና ላንተ ማደግ ነው የምንሰራው በማለታቸው ብቻ እንድትቀበላቸው ሊነግሱብህ የሚሯራጡ ዘረኛ ቡድኖች በስፋት በኦሮምያ ክልል በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ።


ይህም የተፈጠረው ክፉውና ከፋፋይ ለማንም ያልበጀው የኢትዮጵያ አስተዳደር ዘመን ከልጅነታቸው ጀምሮ ሲያድጉ በኦሮሞ አባቶቻቸው ትውፊትና ባህል እንዲሁም ማህበረሰባዊ አስተሳሰብና ስነልቦና ተቀርፀው ሊያድጉ የቻሉ ሳይሆን ከልጅነት ጀምሮ በሚውሉበትና በሚቀርፃቸው ትምህርትቤት፣ በሚከታተሏቸው ሚዲያዎች በሚለቀቁ መርዛማ የመከፋፈልና ዘረኝነት፣ የመጠላላትና መለያየት ሰበካ፣ ወላጆቻቸው ምንም ማድረግ ሳይችሉ ባልፈለጉት ባላሰቡት መንገድ ተቀርፀው፣ የማያባራ አመፅና የከንቱዎች የስልጣን መሳሪያ እንዲሆኑ ባስገደዳቸው ትርክትና ስርአት ውስጥ የተቀረፁ በመሆናቸው ነው። ይህም በኦሮሞነት ስም ከእውነተኛው የኦሮሞ ማንነትና አስተሳሰብ ወጥተው ባልበሰለና ፍሬ በማያፈራ የግልፍተኝነትና ስሜት መንገድ ለእልቂት ህዝቡን እያሰለፉ ይገኛሉ።

ከምንም በላይ የሀይማኖትም ሆነ ባህል አንዳችም ምልክት በልባቸው ሳይኖር ሁሉን ነገር በስጋ እቅድ፣ በሮሮና ብሶት ወይ በጉልበት፣ በዘር በጎራ በማሰብ፣ ስሜትን ብቻ ማእከል ባደረገ አካሄድ ወጣቱንም ሆነ ሰፊውን ህዝብ በማንቀሳቀስ እየሄዱ ይገኛሉ። የስሜት ማእበል በመሆኑ ለነሱ ይመስላቸዋል እንጂ ከድክመት የወረደ የድክመት መንገድ ነው።

አይደለም ለህዝቡ ያንን ሁሉ የምኞት ጫፍ ብልፅግናን ከባዱን ሰላም፣ ደስታ ገነትን ሊያመጡለት ሀይልና ችሎታ ሊኖራቸው፣ ደጋፊ እንኳን ለማሰባሰብ የሰውልጅ ወገንተኝነት ተፈጥሮን ነው የሚጋልቡት።

የወገንተኝነት ተፈጥሮ ማለት፣ ልክ በሰፈር አካባቢ ወይ በከተማ የምንተያየው ግን ሰላም ብለነው የማናውቀውን ሰው ሩቅ በሆነ ቦታ ወይ ከሀገር ውጪ በሌሎች መሀል ስናየው ከዘመድ በላይ በደስታ እንደምንቀራረበው፣ ይሄም አብዛኞቻችንን አጋጥሞን ሀይሉን እንደምናውቀው፣ ወይ የሆነ በቴሌቪዥን የምንሰማው ዘፈን ላይ የሰፈር ወይ የከተማችን ስም ከተጠራ እንዲሁ መደሰትና መነሳሳት እንደሚያድርብን እነዚህም ፖለቲከኞች በዘራቸው እነዚህን መሰል ሀያል የተፈጥሮ ስሜት ላይ ተንጠላጥለው ለድጋፍ ማሰባሰቢያ አድርገው ሀሳብና ፖሊሲያቸው ተሰምቶ ሳይታወቅ እንዲሁ በድጋፍ እንዲጎርፉ አድርጓቸዋል። ይህም የድክመታቸው ጫፍ ነው።

ፍፁም ደካማ ይሁኑ እንጂ፣ ስራ ቢሉት ምንም የማይሰራ 4 አመት ህፃን እንኳን ቤትውስጥ ቢተዉት ሁሉን አጨቀያይቶ፣ አተረማምሶ፣ ሁሉን ውድ እቃ ሰባብሮ ማበለሻሸት እንደማይቸግረው ሁሉ እንዲሁ ለጥፋት የሚያንስ የለምና እነዚህም ዘረኛ ፖለቲከኞች ጥፋት ለመፈፀም ግን ከምንም በላይ ሀይልን የተሞሉ ናቸው። ለኦሮሞ ህዝብም ዘላቂ መልካም ሊያደርጉለት ፈፅሞ ባይቻላቸውም ለሌሎችም የሚተርፍ ከፍተኛ ጉስቁልናንና መከራን ግን ሊያመጡለት ይቻላቸዋል።

እውነት የኦሮሞ አባቶች አላዋቂ ወይ ሞኝ ሆነው ነውን ደግነትን፣ አቃፊነትን፣ ከሰው ከተፈጥሮው መስማማትን፣ የዋህነትን ከራስ በላይ ለሌላው አሳቢነትን ተላብሰው ለዘመናት የኖሩት? በበሰለ ባህልና ማህበረሰባዊ ጥበብ አዳብረው የገነቡት ዘመን የፈጀ ሀብታቸው ነው እንጂ። 


ለምሳሌ አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ ሌላ ቤትም ሆነ አካባቢ የማያውቅ ደሀ ነዋሪ የሆነ የሰው ፍጡር በላይ በዛቦታ ላይ የበላይነት፣ ከሱ የበለጠ ጥቅማጥቅም፣ ቀዳሚነት፣ ንግስና በሰፈሩና በከተማው ይገባኛል እያለ ከጅማ፣ ከወለጋ ዘሩን ብቻ ተማምኖ የሌላውን እየተጋፋ በራስ ወዳድነት፣ አልጠግብ ባይ ጥቅመኝነት፣ በተገኘው መንገድ ሁሉ ተጋፍቶ ራስን ለመጥቀም እያሉ መጋፋትን የሚያክል ክፉ፣ ከባህል ውጪ፣ ከምግባር ውጪነት ከቶ ሊኖር ይችላልን? እንዲህ ያለ ከባህልም ከፈጣሪም የሚለይ ስብእናን መላበስ ምን ትርጉም ይሰጠዋል?

ይህ የራስወዳድ ብልጣብልጥነት፣ ጊዜው ከፈቀደ ከመዝረፍ ከመጋፋት አለመመለስን የኦሮሞ አባቶች በባህላቸው ሳያውቁት ስለቀሩ ነው ያልተላበሱት? እውነተኛ ውጤቱን ስለሚያውቁትና የተሻለውን መንገድ ስለሚያውቁት ነው እንጂ።

በዚህ መልኩ ተሄዶ ምን አይነት መልካም ነገር ይሆን ለኦሮሞ ህዝብ የሚያስገኙት? ለሌላውም የሚተርፍ ውድቀት መከራን ነውንጂ።

ሰፈ ግዛትን? ወይ የአዲስ አበባ ከተማን? ወይ ሀብት? ዴሞክራሲ ነፃነት? ብልፅግናን? ገነትን? እነዚህን አንዱንም ሳይሆን በትንኮሳና ጥላቻ መርዝ መርጨት፣ ከሌላውም ጋር ትርጉም አልባ ደም መፋሰስን ነውንጂ። ይህ ዝምብሎ ፍረጃ አይምሰልህ ያካሄዳቸውን መንገድ ጫፍ ነው የምነግርህና እውነቱን ተመልከተው። ፈልገውትም ይሁን ሳይፈልጉት፣ የያዙት መንገድ መዳረሻ ጫፉ የታወቀ ነውና እውነቱን ልትመለከተው ይገባሀል።
እንደው መሰናክላቸው ሁሉ ጠፍቶላቸው ምኞታቸው ቢሳካ እንኳን ለሀሳባቸው አንዳችም እውነተኛ ዘላዊ መልካም ነገር የማያስገኝ ያልበሰለ ልፊያ ውስጥ ነው ያሉት።

ለነገሩ እነሱም የጀመሩት አካሄድና መንገድ ከኢትዮጵያ የሚለያቸው መሆኑንና ይህም የሚዘጋጁበት መሆኑን ያውቁታል። መዘዙንና ውስብስብነቱን፣ የውጤቱም ጭቃነት፣ የመንገዱንም ምናባዊነት ላንተ አይነግሩህም ወይም አይገነዘቡትም እንጂ። አንድ ቀን በህዝቡ መሀል ያልኖሩበት ችግር ሸሽተው በውጪ የኖሩት በሀገሩ ያለውን ሁኔታ ቀን በቀን አብረው እየኖሩበት ያልተረዱትን አፍ ያገኙ ዘረኛ ቀስቃሾች የሚያራምዱት ሀሳብና ከብሶት ጋር በደካማ መንገድ የሚነዙት ወሬ እንጂ በተግባር ሊሆን የማይችል የውድቀት ሀሳብ መሆኑ ግልፅ ነው።
የኦሮሞ ክልል ህዝብ ከመሀሉ የወጡ በስልጣን ያሉ በሀገራቸው ምድር ታሽተው በህዝቡ መሀል ኖረው በስልጣንና አመሩን መንገድ ኖረውበት ተረድተውት አንድነት ይሻለናል ብለው የሚናገሩትንማ ሊሰማቸው ፈቃደኛ አልሆነም።እውነታውን ውስጥ ሆነው የተረዱት ግን ከምንም በላይ እነሱ ናቸው። ከኦሮሞ ክልል ህዝብ ይልቅ ሌላውን እናስቀድም ብለው፣ ወይ ሌላው ህዝብ ከኦሮሞ ክልል ህዝብ በላይ እንዲወደን እንፈልጋለን ብለው አይደለም የዘመኑ ዘረኛ ጥቅመኛ ፖለቲከኞች የሚሰብኩትን የሚለያይ ነገርን አብዝተው የሚጠየፉት። ውጪ ሳይኖሩበት ከሚጮሁት ይልቅ ኖረውበት እውነታውን ለህዝባቸውም ጭምር የሚበጀውን መንገድ ስለሚያውቁት ነውንጂ።
ሌሎችን አስቀይሞ ተጋፍቶ፣ ከሌሎች አጋጭቶ በግልፅ ወደመለያየት የሚመሩ ተግባራትን በትእቢት የሚሰብኩት እነዚህ የኦሮሞ ምድር ዘረኛ ፖለቲከኞች የሚንደረደሩበት የመለያየት ድርጊት ውጤቱ ግልፅ ነው። በራስወዳድነትና እውር ዘረኝነት ድንበራቸውን ገፍተው በአዲስ አበባ፣ በሰሜን እስከወሎ፣ ከደቡብ፣ ከሱማሌ ግማሽ፣ አእምሮ ያጣ ምኞታዊ ጉዟቸውና ሊያስፈፅሙም የተነሱበት መንገድ፣ እብሪት፣ የጉልበት ግድያ ትጥቅ፣ ትውልድንና ህፃናትን ጨምሮ በዚህ ዘረኝነት ስካር መርዞ መሳሪያ ማሰልጠን ሁሉ አሁን የሚታይ ተግባራቸው ነውና፣ አንተም የማይቀር እውነት የሆነው ውጤታቸውን አስቀድመህ ላታውቀው ይገባሀል።

መሬት ላይ ባለው እውነት፣ በተጠላለፈ በተወሳሰበ ድንበርና ወሰን፣ ገና ያልተሰመሩ ሰው ያልሰፈረባቸው ገደላገደሎች፣ ሜዳዎች ይህ ሁሉ ባለበት ሳይሆን ከዚህ በፊት በግልፅ የተሰመረ አንዲት መስመር ድንበር ባላት ኤርትራ ግጭት እንኳን ከሁለት መቶሺዎች በላይ በአጭር ቀናት ፀጥ ያሉበት ዘግናኝ እልቂት የሚታወስ ነው።
እጅግ በተወሳሰበው በኦሮሚያ ክልል ድንበር ዙሪያ ያውም ከአራቱም አቅጣጫ በሚነሳ ግፊያ ደግሞ ምን ያህል ህዝብ በከንቱ እንደሚረግፍ ለማሰብ የሚያስፈራ ግን ከወዲሁ ግልፅ ሆኖ የሚታይ ዘግናኝ እውነታ ነው። ወደዚህ ግልፅ ሆኖ ወደተቀመጠ ውድቀት ህዝቡን ይዘው የሚንደረደሩት የኦሮሞ ዘረኛ ፖለቲከኞች ያለእውቀትና አቅማቸው ባገኙት ዘር ላይ የተመሰረተ የባዶ ድጋፍ ሰፊውን ህዝብ በእውር አይናቸው ከገደል ሊወረውሩት አይሳናቸውም። ይህን እልቂት ሌሎቹስ በዙሪያው ያሉት የተለያዩ ክልሎች ሰባት ክልሎች የሟቹን ቁጥር ሲከፋፈል የተወሰነ የተወሰነ ይደርሳቸዋል። የሌላኛው ወገን እልቂት ግን ሙሉውን ለአንድ ቡድን የሚቀር ሸክምና ውድቀት ይሆናል።
ሰው ምን ምክንያት ሆኖት ወደዚህ ይሄዳል? በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት በደል ያልደረሰበት የለም። ሁሉም ተጎጂ ነው። ምናልባት ጥንት ያሉት ተበዳድለው፣ ተጎዳድተው፣ ተጨካክነው ቢሆን እንኳን ዛሬ ያለው ትውልድና ህዝብ እንደሆነ በተመሳሳይ ዘመን የተወለደ፣ እኩል ከተወለደ ጀምሮ ሁሉን ግፍ ሁሉን ችግር ሁሉን ደስታ እንዲሁ አብሮ እኩል ያየ፣ ተመሳሳይ መሪዎች የቆሙበት ያደኸዩት፣ ተመሳሳይ ችግር ያለበት የዘመን ወንድማማች ተመሳሳይ የተሻለ እድል ያለው እኩል አዲስ ትውልድ ነው።

ሮሮና ብሶት ጋላቢ ጥቂት ጨለማዎች ካለፈው ጨለማ ቀድተው እያጠመቁ ላያድኑት ይለያዩታል እንጂ ዛሬ ላይ ከትውልዱ እኩል ያልተበደለ፣ እኩል ያልደኸየ ከቶም የለም። ላንዱ የሚመጣ መፍትሄ ለሌላውም የሚሆነው፣ ለሌላው የተገኘው መድሀኒት ለዚህኛውም እንዲሁ መድሀኒቱ የሚሆነው። እንጂ አንዱ ተለይቶ የሚፈልገው ሌላው ተለይቶ ሌላው የማይፈልገው በሀገራችን ባሉ ዘሮችና ክልሎች ከቶ የለም። ይህም ላይኖር ይህን እኩል ከደኸየው መሀል ራስን እየለዩ መሯሯጡ ትርምስና እልቂት እንጂ ከቶ አንዳችም ትርፍ አይኖረውም። አምላክም አይወደውም። ጥቂት ጨለማዎች በስብከታቸው ይረብሻሉ እንጂ ሰማኒያ በመቶ ከሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ገበሬው ሆኖ ሳለ፣ እንደው የአማራን፣ የኦሮሞን፣ የትግሬውን ገበሬና ድሀ ቤተሰቦቹን በኑሮ ደረጃቸው አንዱን ከሌላው የሚበላለጥ፣ የሚለያይ ሆኖ ነውን? ሁሉም በያለበት በድህነት ቤተሰቦቹን ይዞ በተመሳሳይ የኑሮ ደረጃ የሚኖር አይደለምን? እንዲያም ኑሮ ተቸግሮ ይማሩ ዘንድ የላካቸው የራሱ ልጆቹን ሰብስቦ የሚመርዝ ስርአትና በትምህርትቤቶቹ ሳይቀር ጠላትነትን የሚሰብክ ክፉ ነጣቂ ስብእናቸውንና ስነልቦናቸውን ወስዶበት ከሱ ባህልና አኗኗር፣ ከአምላኩ መንገድ ጭምር ተቃርነው እዳ እንዲሆኑ የሚያደርግ ዘረኛ ጠላት ተነሳበት እንጂ።

ለዚህ ሁሉ ቀውስ የዳረገን የእምነታችን ድክመትና ስንቱን ይዞ ያሻገረንን የአምላካችንን ክንድ መልቀቃችን ቢሆንም፣ በትርምሳችን ተጠምደን ይህንን እንኳን እንዳናስተውል ሆነናል። በፍቅር መኖር፣ ራስወዳድነትን መጠየፍ፣ ጥቅመኝነትን መጠየፍ ይህ ሁሉ ለሰማይቤት መግቢያ ብቻ መስሎ ይታየናል፤ ለራሳችን ምድር መድሀኒትነት ጭምር እዚሁ ምድር ላይ መጥቶ መስበትኩን ማን አስተውሎት። ራሱን ብቻ እየተመለከተ የሚያደርገው መወራጨት ሌላውን ሲገፋ ሲያስቆጣ በትእቢቱ ታውሮ ራሱን ብቻ ለማሳደግ የሚሯሯጥ፣ አብሮ የሚኖር ወንድሙን በማይቀይረው ማንነቱ ከሱ ለይቶ አግልሎ ራሱን ሊጠቅም የሚሯሯጥ ሰው የእግዚአብሄርን መኖርና በሀያልነት ያለው ስልጣንን ዘንግቶት ነውን? የክርስቶስ ሌላ ማንነቱ የሆነውን ወንድማዊ ፍቅርን እየናደ የሰው ፍጡርን በማይቀይረው ማንነቱ እያገለሉ መኖር እውነት በእግዚአብሄር ማመኑን ፈፅሞ ትተነዋልንዴ?

ወይ ጭራሹኑ ፈጣሪን እስከነመኖሩ ክደነዋል እንዴ? እንደ ሌሎቹ ፈጣሪ የለም ብለን ነው የምናምነው? አንተስ ይህን የምታነበው መኖሩን ትቀበላለህ? ታዲያ እሱ ካለ፣ ፈጣሪ እሱም የአለም ሁሉ ባለቤት፣ የሀይል ሁሉ ጣራ፣ የሁሉ ወሳኝ ባለቤትና ንጉስ የሆነ እሱ እግዚአብሄርን እርዳታ አንፈልግም? እንዲህ የሁሉ ከሀሊና ባለስልጣን የሆነአንኳኩ ይከፈትላችኋልብሎ ሊረዳን ፈቃደኛ የሆነ ንጉስ በሙሉ ሀይሉ እያለ እንዴት እርዳታውን እንዲልክልን አንጠይቀውም?በዚህ ጭንቅና ችግራችን በበዛ ጊዜ እንዴት በመሀላችን እንዲገኝና ሁሉን እንዲያስተካክልልን ልናስበው ልንጋብዘው አልፈቀድንም? የሱን መኖር ካመንን?

ታዲያ እሱን የሚያርቅን ወንድምን ለይቶ ማበላለጥ፣ ለይቶ የሚያስጠላ፣ ለይቶ የሚያስጠቅም በዘር መሯሯጥን ልንይዝ መረጥን? የክርስቶስን በሰወች መሀል መገኛ ገፁ የሆነውን የማያበላልጥ ወንድማዊ ፍቅርን ከራሳችን ሰብረን አውጥተን አሁን በሚታየው መልኩ ተገኘን?

ታዲያ ምን ችግር አለው እንደምእራብ ሀገሮች በስጋ ትግል ራሳችንን ችለን እስካስኬደን እንሄዳለናየሚል ሰው ሊኖር ይችላል። ነገር ግን የስጋ ትግል የሚባል ነገር ከቶ እንደሌለ አታውቅምን? ሁለት ጎራ ብቻ እንዳለ አታውቅምን?
አንዱ የእግዚአብሄር፣ ሌላው ደግሞ የሰይጣን። ከሁለቱ መሀል የሚባል ቦታ ፈፅሞ እንደሌለ፣ ሊኖርም እንደማይቻል አታውቅምን?

በጎችን እረኛቸው ጥሏቸው ቢሄድ አነፍንፈው ሲከታተሉ የነበሩ አውሬዎች ሁሉ ከቶ ችለው ዝም እንደማይሉ አታውቅምን? ከቶ የትኛው በግ ይሆን ማንም ሳይነካው ሊኖር የሚቻለው?

ምእራባውያን ፈጣሪን ክደው በብልፅግና የሚኖሩት ከሰይጣንም ከእግዚአብሄርም ርቀው ነውን? ጨርሶ ወዳንደኛው ስለተጠቃለሉ ነውንጂ። የተማረከን ወታደር ሲገድል የሚውል ማን ጠላት አለ? ቢያደርግም ሌሎች እጅ እንዳይሰጡ እንቅፋት ይሆንበታል እንጂ ለሱ ምን ጠቅሞት? በብልፅግና በሀብት ቢኖሩ ምን ቸግሮት? እነሱ እንደሆነ አልፈው ልጆቻቸውን የሚሆኑትን ፆታ የማስመረጥ መብትና ነፃነት በህግ ጥበቃ የሚደረግለት ባህል እስከመከተል ድረስ ሄደውለታል፣ ቤቱ ገሀነም እስኪደርሱ ባላቸው ጉዞ ንዳት ስለምን ይነካቸዋል? ከመንገድ ጥለው እንዲጠፉ?
እኛም እረኛችንን ብንገፋው፣ ብናርቀው፣ ጋባዥ የማይፈልገው ርኩስ መንፈስ በነፃነትና ሙሉ ሀይሉ ነግሶብን ይፈነጭብናል። በሀገራዊም ሆነ በየትኛውም ትግላችን ውስጥ ስልጡን ሆንን ብለን ወይ ደግሞ ዝንጉ ሆነን አምላካችንን በመሀል እንዲገኝ ሳንጋብዘው፣ ከህይወትና ትግላችን አርቀነው ብንተረማመስ፣ ጋባዥ የማይፈልገው ሰይጣን በመሀላችን ተገኝቶ የምናያቸውን ነገሮች በሙሉ ያስደርገናል። ለዚህም ነው ዘረኞች በሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚከተላቸው ሞትና ደም ለአፍታ ደርቆ የማያውቀው።

ጥላቻን በልባቸው ይዘው ዘር ለይቶ ጥቅመኝነትን ተዋህደው በዘረኝነት ተሰብስበው ግር ብለው በወጡ ሰወች መሀል ለሰው አእምሮ የሚከብድ አሰቃቂ ነገር ሁሉ የሚከሰተው ስለምን ይመስልሀል? እያንዳንዱን ሰው በተናጠል ብትጠይቀው ከቶ ሊያደርገው የማይችለውን የሚጠየፈውን ነገር በተሰበሰቡ ሰወች መሀል ተደጋግሞ ሲደረግ ለምን ይመስልሀል? በየግል ያላቸው የተሻለ ሰብአዊ አእምሮ ጠፍቶ በጋራ አንድ የሚያደርጋቸው ሰው በቁሙ የሚያስቃጥል፣ ዘቅዝቆ የሚያሰቅል፣ በስለት የሚቆራርጥ በስቃይ የሚደሰት አዲስ አእምሮ በአንድነት ይላበሳሉ እንጂ፤ በዛ የቡድን መንፈስ ላይ መሪነቱን የሚቀዳጀው መሀል ለመግባት ግብዣ የማይፈልገው ክፉ መንፈስ፣ እያንዳንዱ ሰው አእምሮ ውስጥ እንደፈለገው ተመሳሳይ ሀሳብ የማስቀመጥ፣ ትእዛዝ በመስጠት ማስተባበር የሚያስችለው መናፍስታዊ ተፈጥሮውን በመጠቀም አንድ የጋራ አእምሮ አስይዞ በየግላቸው የሚጠየፉትን ቡሀላም የሚፀፀቱትን፣ እንደሌላ ሰው የሚኮንኑትን ተግባር እንዲሁም ሌላም ያለንግግር የተቀናጁ ጥርጣሬዎች፣ ድንጋጤዎች፣ ፍርዶች፣ ያንድላይ ሀሰተኛ ፍረጃዎች በአንድነት ያለንግግር ተግባብተው አሰቃቂ ተግባሮችን በአንድ አእምሮ ያሰራቸዋል። ሌላም ጊዜ በየትኛውም ቦታ ማንኛውም ሰው ክርስቶስ የሚቃወመውን ነገር ሲያደርግ፣ የፍቅር ፍፁም ተቃራኒ የሆነውን ዘረኝነትን ሲሰብክ፣ ራሱን ጋብዞ የሚመጣ መንፈስ ምሁሩን አእምሮ አልባ እስኪመስል ድረስ ተቆጣጥሮ ክፉ ክፉ ያናግረዋል፣ ያሰራዋል። የዚህ አይነት ክፉ ወንድምን ከሌላው መክፈልና ለይቶ ጥቅመኝነትን መስበክ ደግሞ አንዴ ባለቤቱ መንፈስ ከገባበት ነገሩን አራማጁ ሰው እንዳቀደው ኦሮሞና ሌሎች፣ በሚለው ክፍፍል ፀንቶ የሚያበቃና በዛው የሚቀጥል ሳይሆን አንዴ የክፍፍልና የወገንተኝነት መሪ መንፈስ ካስገቡት ልክ ከላይ እንደመቱት መስታወት ከዋናው ስንጥቅ መስመር ተከትለው ሌላ የበዙ ክፍልፍሎችና ስንጥቅጥቅ እስከጥጋጥጉ እንደሚዛመት፣ ኦሮሞ ወይ አማራ ብለው ክፍልፍልን መርጠው ከላይ ራሳቸውን የከፈሉበት መንፈስ ወርዶ የወለጋ ኦሮሞ፣ የአርሲ ኦሮሞ እያለ እየቀጠለ መጨረሻ የሌለው ነቀርሳ መንፈስ መሆኑ የሚወራ ሳይሆን በተግባር የሚታይም መገለጫው ነው። ቀድሞስ ቢሆን በዚህ መሀል የሚነግስ መንፈስ ከዛ ዘር ወይ ከሌላው ዘር ምን የተለየ ጉዳይ አለውና? በቻለው መጠን የልዩነትና ባላንጣነትን፣ ወገን ለይቶ ጥቅመኝነትን መንፈስ አንግሶ ፍቅርን እስከተቻለው መጨረሻዋ ቅንጣት መስበር ነውንጂ። በፍቅር የሚመሰለውን ክርስቶስ የወንጌል ህሉ ጭምቅ መልእክት በፅኑ መዋጋት ነውንጂ።

ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረውትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ምን ባለመንፈሳዊ ፀጋ ባለቤት፣ ምን ባለቅዳሴ፣ ባለማህሌት ብንሆን፣ ሁሉ በዜሮ ተባዝቶ እምነት ከሌላቸው ሀጢያተኞች ጋር በአንድ ላይ እንወድቃለን።

ሀገራችን ከፊቷ የቆመው መከራ ግልፅ የሆነ ነው። ከክፋቱና ስፋቱም የተነሳ ከሌሎቹ ይልቅ በትንቢት መፅሀፍት ተዘርዝሮ የተገለፀ ሆኗል። በትንቢት ተገልጦ በብዛት መፃፉም መነገሩም፣ በኛ በሰይፍ ወዳቂዎች ላይ ቀድሞ ለመዘባበት ወይም ደግሞ ካለፈ በኋላ ቃሉ መፈፀሙን ያዩ አማኞችን ለማስገረምና ማስደነቅ ታስቦ ሳይሆን በአሁኗ ሰአትና ደቂቃ ከደጃፉ የተሰለፍነው የእግዚአብሄር ልጆቹ አይተን እንድንበትና መከራውን እናልፍበት ጊዜውን እናሳጥርበትና እንተርፍበት ዘንድ ነው።
ይህንንም ማድረግ የምንችለው ከሁሉ ቅድሚያ የአምላክን በመሀላችን መገኘት በመናፈቅና የሚጠየፋቸውን ማንኛቸውንም ነገሮች ከመሀላችን በማራቅ ለሱ ጋባዥ በመሆን ነው። አምሳሉ የሆነውን የሁሉን ፍቅር አጥፍተን ዘረኝነትንና ከሌላው ተለይቶ ጥቅመኝነትን እስካልተውን ድረስም ይኸው ተግባር ግብዣው የሆነ ሌላው አካል ነግሶብን ትግል ኑሯችን መከራ ህይወታችን ሆኖ በጭቃ እየዋኘን ዘመናትን እናልፋለን። በዚህም ምክንያት ከየትኛውም ምድራዊ ትግላችን ፊት የእግዚአብሄር ህግ ከሁሉ በላይ አፅንተን መሰረት በማድረግ፣ ራሳችንን አስገዝተን እሱ በመሀላችን መሆኑን እናረጋግጥ፣ ከዛ በኋላ ባለው ማንኛውም እንቅስቃሴያችን እሱም ስህተቱን አርሞ፣ በጎደለው ሞልቶ፣ ያላሰብነውን ፈፅሞ የትኛውም ጠላት የማይቋቋመን ድል አድራጊዎች እንሆናለን፣ ለራሳችን አልፈን ለሌላው የህይወት ደስታ እንሆናለን። ችግሮቻችን ላንለያቸው የፈለግን ይመስል ስንዘምራቸው ስንደጋግማቸው የምንኖር ሳንሆን ሁሉ ተፈቶልን በሰላም የምንኖር እንሆናለን። ስለዚህም ያንተ ምርጫ አምላክህን ማስቀደም፣ በልጅት ሆኖ ከሚመጣው ሁሉ ይቅርታን ጥበቃን በመለመን የፀና ይሁን። ከሁሉ ዘረኛና እንቅስቃሴያቸው ራስን አግል። ከሌሎች ወንድሞችህ ጋር ግንኙነትህን አጠንክር አስፋ፣ በእኩልነትና ፍቅር ኖረህ አምላክህን አስቀድም፤ እሱን በርትተህ ያዝ። በምታደርገው ቀሪው የምድር ትግልህ ጠላቶችህ ከደጅህ ሳይደርሱ በቦታቸው ተነው ይደመሰሳሉ። አምላኩን ትጥቁ እንዳደረገው ንጉስ ዳዊት በዘመትክበት ሁሉ ካንተ ቀድሞ ድል በሜዳው ይጠብቅሀል።

ኢትዮጵያዊነት እንዲሁ በባንዲራ የሚገለፅ፣ ወይ ደግሞ በዘረኞች አንደበትተወሮ የተያዘ ምድር መጠሪያ ወይ ደግሞ የአፍሪካ አንድ ሀገር ቅርፅ፣ ተብሎ እንደሚነገረው አድርገህ አትየው። ይልቁንስ ከቀድሞም መነሻው በነበረው ፍልስፍና፣ የዥንጉርጉሮች በክርስቶስ አምሳል ሰብአዊነታቸው ብቻ በአንድነት በፍቅር የሚኖሩበት፣ እግዚአብሄር በፈጠረው ዥንጉርጉር ፍጥረት መሀል የሚገኝበትን የፍቅርና አንድነትን መልክ መላበስ በመሆኑ ብቻ እየው።
እግዚአብሄርን የረሱ ስልጣን እጅግ ያፈቀሩ ታጣቂዎች ህብረት በድህነትና ፍቅር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መሀል ከፍለውኦሮሚያ ክልልየተባልክ መሆንህን አትርሳ! ኦሮሚያ ተብሎ የተከለለው ምድር ኢትዮጵያዊ መሆንህን አትርሳ ! ለልጁተመልከት ያንተን ንብረትብሎ አክሱም የሚጠቁም፣ተመልከት ያንተን ሀብትብሎ ጣናን፣ አባይን የሚጠቁም፣ ተመልከት የርስትህን ጫፍብሎ ከካርታ ላይ ኦጋዴንን የሚያሳይ፣ እሱራሱ እንዲህ ተብሎ ከአባቶቹ የተረከበውን እንዳባቶቹ ታግሎ ጠብቆ ለሚወደው ልጁ ሙሉ መብትና ባለቤትነትን የሚሰጥ ነህ።

አባቶቹ ደማቸውን ከፍለው የገዙትለትን ጥሎ ጠቦ የሚሸጎጥ፣ ከፍተኛ ቁጥርን ይዞ ሳለ፣ ከንቱ ስልጣን ፈላጊዎች በዘረኝነት፣ በሮሮ፣ ዘላለም የማይለቅ የተጎጅነት ትርክት በማልቀስ የሚጠምዱት፣ ዘግናኝ እልቂትን አልፈው ራሳቸውን አሳድገው ታላቅ እንደሆኑት እስራኤላውያን ሳይሆን፣ ዘላለም ሮሮ በመደጋገም፣ ተጎጅነትን በመተረት፣ የዘር ተጠቂነትን በማላዘን ሳይቀየሩ እንደኖሩት ጥቁር አፍሪካውያን እንድትሆን የሚያደርጉህን የምትከተል አትሁን። ትልቅ ቁጥርና ተፅእኖ ፈጣሪነትን ይዘህ ሳለ፣ ጥቂቶች ስልጣንን በመፈለጋቸው ብቻ፣ ሌሎች አናሳዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ሊጎዱን ነው፣ እንዲህ ሊያደርጉን ነው በሚል ከንቱ ለቅሶ የያዙ የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው ጠባቦች የሚያሽከረክሩህ ሳይሆን፣ በሰፊ ሙሉ ቁመና ያለህ ትልቅ መሆንህን ተማምነህ በፍቅር አንድነት ክብር የምትኖርባትን የእግዚአብሄር ምድር ኢትዮጵያን የሚያድነው ኢትዮጵያዊ እንዳትሆን ከቶ ምን ያንስሀል?

በኢትዮጵያ ይመጣል በተባለው መከራ፣ በየትኛውም በኩል ያሉ ዘረኞች ከየትኛውም ዘር ይሁኑ በቅስፈት ይመታሉ፣ እርስበርስ ይወድቃሉ። እግዚአብሄርም የዚህን ዘር ብሎ ከክፉ ከዘረኞች መሀል አንዱን ወዶ አይመርጥም፤ ማንኛውም አንዱን ወንድሙን ከሌላው ከፍሎ ለይቶ ጥቅመኝነትን የሚፈልግ፣ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነውን መስፈርት አልባ ወንድማዊ ፍቅር ላይ የተነሳ ሁሉ በአንድነት ይወድቃል። እናም ተነስተህ ድል በሚሆንህ ፍቅርና አለመገላለል፣ አለመመራረጥ ሆነህ ከአምላክህ ከሌሎች ከየሁሉም የሆኑ ወንድሞችህ ጋር በህብረት ሆነህ አምላክህን ከሚመጣው ሁሉ ያድንህ፣ በፈቃዱ ያኖርህ ዘንድ በመማፀን ፅና፤ ከሚመጣው መከራ ሁሉ እንዲጠብቅህ ቅረበው።

መፅሀፉ እንዳለው፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር ኦጆችህን ወደእግዚአብሄር ዘርጋ።የተተነበየው የሚመጣው መከራና እልቂት ያለንሰሀ በሀጢያት ጨቅይተው በመጣባቸው አልፎም አሻፈረኝ ብለው በተነሱ የፍቅር ተቃራኒ ፅልመት የሆነ ዘረኝነትን በተላበሱት መሀል፣ እንዲቀር፣ የነሱ ጉዳይ ይሆን ዘንድ፣ አንተ ራስህን አንፃ አድን። ሀገርን ለማዳን በከንቱ ምድራዊ ፖለቲካ ልፊያ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሄርና በሱ መንገድ ላይ ትጋ። እውነትም አለና፣ እንደ ልጁ ሆነህ፣ እጄን ያዘኝ በለው። ድህነት ከሀጢያት ለነፁት እንጂ የሆነ ፖለቲካ አቋም ለያዙት አይደለምና፣ በንሰሀ ታጥበህ ራስህን ከሀጢያት ጠብቀህ ዘወትር ድህነቱንና ይቅርታውን በመለመን ተዘጋጅተህ ኑር። ስለዘራቸው፣ ስለ ፖለቲካቸው ሳይሆን ስለ ፍቅርና እግዚአብሄር ልጅነታቸው ባመኑት እግዚአብሄር ተጠብቀው ከሚተርፉ ጥቂቶች መሀከል ሁን። 


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment