ትላንት የአይሁዶች አዲስ ዓመት የሚጀመርበት ዕለት ነው፤ (የ ሥነ–መለኮታዊ ዓመት መግቢያ የመጀመሪያው ሰንበት)፥ ኒሳን ፩ (የወራት መጀመሪያ) / 5779
እስራኤል በጉን እንዲያርዱ የታዘዙበት ወር ኒሳን ሲሆን በእኛ ሚያዚያ መሆኑ ነው። በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ነውር የሌለበት ማለትም ጠጉሩ ያላረረ፣ ቀንዱ ያልከረከረ፣ ጥፍሩ ያልዘረዘረ፣ የአንድ ዓመት ጠቦት እንዱያዘጋጁና ወሩ በገባ ከ አሥረኛው ቀን እስከ አሥራ አራተኛው ቀን አሥረው በአሥራ አራተኛው ቀን እንዲሠውት ታዘዋል፡፡
የዚህ ምሳሌነቱ ነጥብ የምታክል ነውር የሌለበት ማለትም ምክንያተ ኃጢአት የሌለበት ንጹሐ ባሕርይ ጌታ በቅንዓተ አይሁድ ታሥሮ፣ በመስቀል ላይ ራሱን ለመሠዋቱ ምሳሌ ነው፡፡
በርሊን የፀረ–ክርስቶሱ መቀመጫ ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ ናት። ራዕይ ዮሐንስ ላይ ከተጠቀሱት ሰባት ዓብያተ ክርስቲያናት (ሁሉም ያሁኗ ቱርክ ውስጥ ነው የሚገኙት) መካከል አንዷ፤ ጴርጋሞን ናት፤ ይህችም የሰይጣን ዙፋን የሚገኝባት ቦታ እንደሆነች ቅዱስ ዮሐንስ ጠቁሞናል።
ታዲያ ከ ጴርጋሞን የተወሰደው የሰይጣን ኃውልት አሁን የሚገኘው በበርሊን ከተማ ነው። እነ ሂትለር፣ ቡሽ፣ ኦባማና ክሊንተኖቹ ሁሉም ይህን መሰዊያ ለመሳለም ወደ በርሊን ጎራ ብለው ነበር። ስልጣን ሱስ የሆነባት ወይዘሮ አንጌላ ሜርከልም ከዚሁ የሰይጣን ዙፋን ፊት ለፊት ነው የምትኖረው። በዛሬው ዕለት ደግሞ ባራክ ሁሴን ኦባማ ይህን የሰይጣን ዙፋን ለመሳለም ወደ በርሊን በድጋሚ መጥቷል። በተለያዩ ምክኒያቶች ለአሥረኛ ጊዜ ሲጎበኝ ነው። "ዙፋኑ ሱሴ ነው!"
[ የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፪ ]
፲፩ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም ።
፲፪ በ ጴርጋሞን ም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል ።
፲፫ የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም ።
፲፬ ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ ።
#ዘርአዳዊት_ዘ_ኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያ_አውታር
#ሰላቢ_እጆች
Blogger Comment
Facebook Comment