እንኳን ለአለሙ ቤዛ ለቸሩ መድሃኒዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!



የመድሃኒዓለም ሞት በሚታሰብበት ክብረ በዓል እርሱ ለስው ልጅ የሰጠው ስጦታና ሃብት/ጸጋ/ መነገር አለበት፡፡ ለምን ሞተ? ሰው በኃጢአቱ ምክንያት ሞት ይገባው ነበር፡፡ ለሞቱም እዳ የበጎችን ደም ይከፍል ነበር፡፡ 

ይህ ብዙ የገንዘብና የሞራል ኪሳራ ነበረው፡፡ በጎቹም ከሞት በኃላ በአምላክ ችሎት ለነበረው ተጠያቂነት አይሆኑም ነበርና ፍርዱን ለመክፈል ወደ ሲዖል ይጣል ነበር፡፡ ጌታ ሲሰቀል ለሰው ሁሉ ዋጋ ከፈለ፡፡ ኃጢአት የከሰሰው ሰው እባብ የነደፋቸው እስራኤል ወደ ነሃሱ እባብ እንደሮጡ ወደ እርሱ በእምነት ከመጣ ይቅርታ ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ተከፍሎላቸዋልና፡፡ 

ክርስቶስ ተሰቀለ ብቻ ሳይሆን እዳዬን ሊከፍል ተሰቀለልኝ ማለት በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ጽድቅ ነው፡፡ ሰው ከአምላክ ጋር ሰላም የሚሆነው ደሙ የነካው እንደሆነና ለተከፈለው ዋጋ ትኩረት ሰጥቶ ሲያመሰግን ሲመሰክር ነው፡፡ መቅሰፍት ደሙን ካየ ገለል ብሎ ያልፋል፡፡ መድሃኒዓለም የሞተው ሰማይ ተከፍቶ እንድንገባ ነው፡፡ ዛሬ ከርሱ ጋር በገነት እንድናድር ነው፡፡ ሉቃ 23:43 ልጁ ወደ መስቀል የሄደው ሁላችን ልጅነት እንድናገኝ ነው፡፡ ገላ 4:4 

ስለዚህ ይህ በዓል የከበርንበት፣ ምህረት ያገኘንበት፣ የተፈቀርንበት፣ እዳችን ተከፍሎ ከእስር የተፈታንበት በዓል ነው፡፡ ከልደት፣ ከጋብቻ፣ ከፍቅር፣ ከብሄራዊ በዓላችን በላይ ነው፡፡አቤቱ ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ፡፡


የቀራንዮ ንጉስ ቸሩ መድሐኔዓለም ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment