የ አውሬው 666 መሳርያ የሆነው በ5G ኔትዎርክ የሚሰራ ስማርት ስልክ ሳምሰንግና ቬራይዘን በጋራ ሰርተው ገበያ ላይ ሊያውሉ ነው



ሳምሰንግና ቬራይዘን በ5G ኔትዎርክ የሚሰራ ስማርት ስልክ በጋራ ሰርተው ገበያ ላይ ሊያውሉ ነው

ሁለቱ ኩባንያዎች የስማርት ስልኩን የመጨረሻ ንድፈ ሀሳብም በዚህ ሳምንት በሚካሄደው የኩዋልኮም ስናፕድራጎን ጉባዔ ላይ እንደሚያቀርቡትም ተነግሯል።
በ5G ኔትዎርክ ይሰራል የተባለው ስማርት ስልክ ገና በገበያ ላይ የሚውል አዲስ ኩዋልኮም ፕሮሰሰር የሚጠቀም መሆኑም ነው የተገለፀው።

ኩባንያዎቹ በሰጡት መግለጫም የ5G ኔትዎርክ ስማርት ስልኩ የሳምሰንግ ኔትዎርክ መሳሪያዎችን በመጠቀም የተሰራ የዓመታት ጥምረት ውጤት ነው ብለዋል።

በርካታ ኩባንያዎች 5G ኔትዎርክን ስራ ላይ ለማዋል እየተሯሯጡ ሲሆን፥ ሳምሰንግ እና ቬራይዘን በጥምረት ሊሰሩት ያሰቡት ስማርት ስልክም ይህንን ኔትዎርክ ማስተናገድ የሚችል ነው።

አዲሱ 5G ኔትዎርክ ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ በሚውልበት ጊዜ አሁን ካለው 4G ኔትዎርክ በፍጥነት እና መረጃዎችን በማውረድ (ዳወንሎድ) የማድረግ ፍጥነቱ ከፍተኛ መሆኑ ተነግሮለታል።

ምንጭ፦ fossbytes.com
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment