ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የማርያም መቀነቱን ምልክት ላለማየት፣ የነጎድጓዱን ድምጽ መልዕክት ላለመስማት አሻፈረኝ እያሉ ነው፤ የእንግሊዙ ጋዜጠኛ ትዕቢትና ግትርነት “የ ሌባ ዓይን ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ!” ያሰብላል።
“ኤግዚቢሽኑ የተዘጋጀው በለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጋር በመመካከር ነው....መብታችን ነው፡ ኢትዮጵያ እንደ ኢራቅና ሶርያ ህግ አልባ ልትሆን ስለምትችል እዚህ መቆየት አለበት....ቅብርጥሴ.”
ምን እያዘጋጁልን እንደሆነ ልብ በሉ!
የቀማኞቹ የዔሳውና እስማኤል ዘሮች እኛን ከማታለል፣ እርስበርስ ከማዳቆስና ከማባላት አያርፉም...
ትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ ፪:
፩ በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።
፪ በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፤ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፤ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።
፫ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፤ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።
፬ በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፤ እነርሱም። ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፤ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።
፭ ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።
፮ ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፤ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።
፯ የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?
፰ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፤ ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፤ ሳይፈሩም፤ የሚያልፉትን ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።
፱ የሕዝቤንም ሴቶች ከተሸለሙ ቤቶቻቸው አሳደዳችኋቸው፤ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘላለም ወሰዳችሁ።
፲ በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፤ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።
Blogger Comment
Facebook Comment