በከበደ ገሠሠ
ቋንቋ:- በሁለት ወይም ከዚያም በበለጠ ባሉ ወገኖች መካከል ለግንኙነት የተፈጠረ የማይናገር “ግዑዝ” አካል ነው። ስለሆነም ቋንቋ የትኛው ወገን (ዘር) ሌላውን እንደገዛ የሚያመለክ\ት አይደለም፤ በሌላ አነጋገር አንድን ዘር ወደሌላኛው የመለወጥ ኅግም ሆነ ሥርዓት የለውም።
ለወያኔ፣ አማርኛ ቋንቋ መጥፋት የአማራን ታሪክ፥ የስነጽሑፍ ሀብትና ማንነት ለማጥፋት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው ብሎ ያምናል። በዚህም መሰረት በተለያየ አሰላለፍ ቋንቋውን ማመናመን የሚችሉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ታቅደው ከሞላ ጎደል ተከናውነዋል።
1 . ከሀገር አቀፍ የጽሑፍ አገልግሎቱ መሸርሸር የመጀመሪያው አሰላለፍ ሲሆን፣ በዚህም የራሱን የቋንቋውን ይዘት በማወክ ምሉዕነቱን ማሳጣት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ነበር። ጽሕፈቱን ይጠቀሙ የነበሩ ቋንቋዎችን አንዳንዶቹን በላቲን ፊደል እንዲጠቀሙና ሌሎቹንም ደግሞ የየራሳቸው ፊደል እንዲቀርጹ በማዘዝ አማርኛ እንዳይጠቀሙ የተደረገበት ሁኔታ ነው።
2. ሁለተኛው አሰላለፍ አማርኛ ከንግግር አገልግሎት የሚጠፋበትን መንገድ በመቀየስ ሥር የሰደደ የአሰራር መዋቅር መፍጠር ነው። አማርኛን የጋራ መግባቢያ አድርገው የኖሩ ማህበረሰቦችን በየብሔር አስተዳደሮቻቸው መዋቅር የባህል እና ቋንቋ ልማት እንደ አንድ ሴክተር ተይዞ በዋናነት አማርኛን ትተው የራሳቸውን ቋንቋ ስለመጠቀም ግዴታዊ ግንዛቤ የማስረዕ ስራ ተከናውኗል።
እዚህ ላይ ትኩረት እንዲሰጠው የሚያስፈልገው፣ የራስን ባህልና ቋንቋ ማልማት የተቀደሰ ተግባር መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ነው፤ ይሁን እንጅ ብሔረሰቦች አማርኛን እንዳይጠቅቀሙ ለማድረግ የተሸረበው ሴራና ተግባራዊነቱ በታሪካችን ለምንጊዜም የማይጠፋ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ አሳፋሪ ተግባር መሆኑ ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም።
“ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል”እንደሚባለው፣ ከወያኔ ቀጥሎ የመጣውም ብልጽግና/የኦሮሙማ መንግሥት ተመሳሳዩን መንገድ በመከተል እንዲያውም በበለጠ ሁኔታ አማራውን እንደ ማኅበርሰብ ብቻ ሳይሆን ቋንቋውንም ከብኄራዊ መገልገያነት በማውረድ እንዲመነምን፣ ብሎም ጨርሶ እንዲጠፋ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ግን፣ አይሳካለተም ! አማርኛ የሕዝቦች ቋንቋ ሆኗል፡፡ ከሀገሪቱ 125 ሚሊዎን አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥ 90% አማርኛ ተናጋሪ ነው፤ ስለሆነም፣ ማንም ወደደ ጠላ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ህብረ-ብሔራዊ እሴታችን; አንዱ ዋና የመገናኛ ድልድያችን አማርኛ ቋንቋ ነው፡፡ አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት መሞከር የድፍን አውሮፓውያኑን “ላቲንን/Latin” ከመላው ዓለም ለማጥፋት እንደመሞከር ያህል ነው። ዓባይን በጭልፋ! እንዲሉ፡፡
ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው ባሁኑ ወቅት በመንግሥት ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ ያልትቋረጠ በደል እየተፈጸመበት ይገኛል፡፡ ሌላው ቢቀር በወያኔ መንግሥት ጊዜ “ዐማርኛ የፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል” ሲል የተደነገገውን፣ ባሁኑ የኦሮሙማው/ብልጽግና መንግሥት ግን ቦታ አልተሰጠውም፡፡ ምክንያቱስ ቢባል፣ መልሱ “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ነው፡፡
የቋንቋው መበላሸት ሆን ተብሎና ዐውቆ ወይም ባለማወቅ
አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት በወያኔ የተጠነሰሰው እኩይ ዓላማ፣ በንግግር ጊዜም ሆነ በጽሁፍ ሥርዓትን ያልተከተለና የተበላሼ ቋንቋ እየሆነ ስለመምጣቱ ጉልህ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከቃላት እስከ ዕለታዊ አነጋገር አያሌ ስህተት እየተፈጸመበት ነው፤ ለመነሻ እንዲሆነን የቃላቶች ግድፈት ወይም ለውጥ ቋንቋውን በማያውቁ ተናጋሪዎች ሳይሆን ሆን ተብሎ በመንግሥት ደረጃ ቁንቋው እንዲጠፋ ወይም የተናጋሪው ብዛት እንዲቀንስና በደረጃም በሀገሪቱ ከሚነገሩት ቋንቋዎች የበታች እንዲሆን የሚደረግ ሴራ መሆኑን ለመረዳት ብዙ እርቆ መሄድን አይጠይቅም፡፡
ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ፣ ጋዜጠኞችና የማኅበራዊ መገናኛ ዜና አቅራቢዎች ጭምር ቋንቋውን መሠረት ባደረገ የጥያቄና መልስ ወቅት ግድፈት ወይም ስህተት ሲድረግ “. . . እንደዚህ ማለተህ/ማለትሽ/መለትዎት ነው?” ብሎ ስህተትን ለማረም የሚደረግ ጥረት አለመታየቱ ነው፡፡
የሚከተሉት እንደማሳያ የቀረቡ ግድፈቶችና እርምት የተደረገባቸው ቃላቶች ናቸው፤
ሰንጠረዡን እንመልከት፦
ትክክል ያልሆነ መሆን ያለበት/ትክክል አስተያየት አስተያይት
ድጋፎትን ድጋፍዎትን
(የ ESAT) ማስታዎቂያ)
አዲስ አቦች/አበቦች
አዲስ አበቤዎች/ አበቦች
መዋለህፃናት
መዋዕለ ህፃናት
(ት መ ማ ድ) ትም/ሚኒስቴር)
ስሞት ማነው?
(ስምዎት/ስመዎት ማንነው?)
ሂወት”
ሕይዎት
ትገርማለክ
ትገርማለህ
ሶዬው
ሰውየው
ዶሮዋ ታስፈልጎታለች
ዶሮዋ ታስፈልግዎታለች
ከሚመሩት “መንግሥቶ”
ከሚመሩት መንግሥትዎ/ት
መንፈሳይ
መንፈሳዊ
ተጋብጄ
ተጋብዤ
ነብስ
ነፍስ
ፈጣሪ ይጠብቃቹ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ
ብለክ ብለክ ኢህንን አመጣክ? ብለህ ብለህ ይህንን አመጣህ?
ምውለው ምያድረው
የሚውለው የሚያድረው
ጥያቄችን
ጥያቄያችን/ጥያቄዎቻችን
መልስ እንድጽፍሎት
መልስ እንድጽፍልዎት
እንዲለቀቅላቹ
እንዲለቀቅላችሁ
እንግዲህ ከዚህ በላይ በሰንጠረዙ እንደተመለከትነው፣ <አማርኛ “በእግሩ ሂዷል”> የሚያስኘውን ዘይቤ በገሀድ ያየንበት ነው፡፡ ጥያቄው? አሁን ካለበት ደረጃ ወደባሰ እንዳይሄድ የመግቻ መንገድ ይኖረዋል ወይ? ነው፥
መልሱ፣ የቋንቋው ባለቤት የሆነው አሁን ያለው ትውልድ ብቻ ሳይሆን፣ ሌላውም በመላው ዓለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ፣ ምሁሩ፣ ፖለቲከኛው፣ ተማሪውና ስደተኛው፣ አማርኛ ቋንቋ ሥርዓቱንና ይዘቱን ጠብቆ እንዲገኝ ማድረግ ይቻል ዘንድ ክፍተኛ ርብርቦሽ ማድረግ ይጠበቅበታል ነው፡፡
ሀ/ [የአማርኛ ቋንቋ ቀደምትነት፦
የአማርኛ ቋንቋ ከክርስቶስ ልደት 120 ዓመት ቀድሞ በኢትዮጵያ በስፋት ይነገር እንደነበር ግሪካዊው የታሪክና የመልክዓ ምድር ተመራማሪ “Agatharkides አጋታርኪደስ” ትቷችው ካለፈ በርካታ መጻህፍት ፟ኤንስይክሎፔድያዎችን ጨምሮ፣ እርሱን እየጠቀሱ ያማርኛን ምንጭ ከክክርስቶስ ልደት በፊት መሆኑን ይመሰክራሉ፤
ለ/ አማርኛ በቴክኖሎጂ ጎዳና
አማርኛ ጥንታዊ ብቻ ሳይሆን፣ ከቴክኖሎጂ ጋር አብሮ የሚሄድ ዘመናዊ ቋንቋ መሆኑን በልዩ ልዩ የምሁራን/ሊቃውንት ጉባኤ ላይ ተደጋግሞ ተገልጿል።
ሐ/ አማርኛ ቋንቋ በሚከተሉት የአሜሪካ ኡኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፤፟
Boston University,
Harvard University,
MSU, (Michigan),
Stanford University,
UCLA,
UC (San Diego),
UF (CA),
UPenn, University of Pittsburg.
Blogger Comment
Facebook Comment