የዋቄፈታ አምልኮ ተከታዮች በሚሊዮን ስላሉ አንድ አንድ አስገራሚ እውነቶችን ስለ ዋቄፈታ ላጋራችሁ ወደድኩ።
በሰለሞን ሺፈራው ተጻፈ!
ዋቃ(Waaqa)ምን ማለት ነው?
የሁለት ቃላት ጥምረት ውጤት ነው።
Waa፦jechuun waan wa'ii jechuudha.(የሆነ እንደማለት ሲሆን)
Haaqa፦jechuun immo waan dhugaa ta'e jechuu dha.(እውነተ እንደማለት ነው)
ትርጉሙም የሆነ እውነተኛ ወይም ትክክል ወይም Waaqa ይባላል።
~
፪፦ሃይማኖቱን ደግሞ ዋቄፈና (Waaqeffannaa) ብለው ሰየሙት።
የዚህም ቃል ስያሜን ስንመለከት ለሁለት ይከፈላል።
Waaqa እና anfana ተብሎ። ዋቃ የሚለው የመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየዋችሁ እውነተኛ የሁሉ ፈጣሪ የሆነ እንደማለት ነው። anfana ማለት በራሳችን እንጠራለን ወይም ራሳችንን እናቀርባለን ማለት ነው።
~
፫~ዋቄፈታ ከሌሎች ሃይማኖቶች የሚያመሳሰልበት ነገር ምንድነው?
፦ዋቄፈታ ከአብዛኞች ሃይማኖቶች የሚያመሳስለው በብዛት ዋቃ(Waaqa) የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው ብለው ያምናሉ።
~
ልዩነት
ዋቄፈታ ብዙ ልዩነት አለው ከሌሎች ሃይማኖቶች። ለምሳሌ እንኳ የሚከተሉትን መመልከት በቂ ነው፥
~
1፦በዋቄፈና ውስጥ ሰይጣን ብሎ ነገር የለም
በሌሎች ሃይማኖቶች ለክፉ ድርጊት መነሻያ ሰይጣን ነው የብሎ የሚታመነው በዋቄፈታ ተከታዮች ዘንድ አይሰራም።ዋቃ ብቻ ነው ያለው ሰይጣን የለም ክፉ ብናደርግ ወይም ከሰው ብንጣላ ሰይጣን ሳይሆን ያጣላን የተፈጥሮ ህግ ነው ይላሉ።
~
2፦ሌላኛው የዋቄፈታ አስገራሚ ነገር ገነት ወይም ሲዖል የሚባል ነገር የለም።
መልካም ብታደርጉ ለፈጣሪያችሁ እንደ ትዕዛዙ ብትገዙ ገነት ትገባላችሁ፣ ነገር ግን መጥፎ ብታደርጉ ለፈጣሪ ቃልም ባትገዙ ወደ ሲዖል ትጣላላችሁ...በእሳት ዲኒ ትቃጠላላችሁ የሚል አስተምሮ ለዋቄፈታ አይሰራም።ምክኛቱም በዋቄፈቶች አመለካከት ሞት ልክ እንደ ውልደት የተፈጥሮ ህግ ነው።
ለምን እንሞታለን ብሎ ዋቃን መጠየቅ አይቻልም። ለምን እንደሚገድለንም ከእሱ በቀር ማንም አያውቅም።
~
3፦በዋቄፈታ ውስጥ ምንም መልካም ብትሰራ ወይም ምንም መጥፎ ብትሰራ ከሞት በኃላ የምትጠቀምበት ነገር የለም።ስለዚህ እንደ ሌሎች ሃይማኖቶች ኃጢአት ብሎ ነገር የለውም።መጥፎ የሚሰራ የማህበረ ሰቡን ህግ የሚጥስ ነው ልክ እንደ ኃጢአት የሚቆጠረው።ይህን የሚያደርግ ሰው ደግሞ የዋቃ ሐይል ያጣል ተብሎ ይታመናል።
የዋቃ ሐይል ከራቀው ክፉ እድል ሊያጋጥመው ይችላል።
~
4፦በዋቄፈታ ሃይማኖት መሰረት አንድ ሰው የሌሎውን አካል እስካላጎደለ ድረስ ፈጣሪ(ዋቃ) ሐይሉን አይነሳም።አካል ሲጎድል ነው ዋቃ ሐይሉን የሚከለክለን ብለው ያምናሉ።
~
5፦እንደ ዋቄፈታ አተያይ ዋቃ ተብሎ የሚያምኑበት የዓለም ሁሉ ህዝብ ከእኔ ሌላ አያምኑም ብሎ ነው የሚያስበው።
~
6፦ዋቃ የሚሉትና የሁሉ ፈጣሪ ነው የሚባለው፥
አልወለድም፣ አይሞትም፣ አይበላም፣ አያረጂም፣ ከሞት በኃላም እድሜ ልክ አይታይም፣ ለዘላለም እንዲሁ ይቀጥላል እንጂ ምድር ትጠፋለች ብሎ ነገር የለም፣ ዋቃን ማሳዘን ወይም ማስከፋት አይቻልም፣ ምንም መጥፎ ብንሰራ የሰው አካል ካላጎደልን ችግር የለውም።የሰው አካል ቢጎድል እንኳ ኃጢአት ሰሩ ሲዖል ይገባሉ ብሎ ነገር የለም።
እዚሁ በምድር ላይ ነው ሁሉ ነገር የሚጠናቀቀው።
Blogger Comment
Facebook Comment