በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር ያለ አንድ ማህበር የኢትዮጵያ መንግስት በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ላይ አሳይቶታል ያለውን ዝምታ አወገዘ። ማህበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት የተሰኘው ይሄው ማህበር ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ መንግስት ጠንካራ ህግ ሊያወጣ ይገባል ብሏል።
የማህበሩ ሰብሳቢ መምህር ደረጀ ነጋሽ እንደተናገሩት መንግስት ለጉዳዩ ላይ ያለው ግዴየለሽነት ለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ንቅናቄ መስፋፋት ረድቷል። ሰብሳቢው በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንዲስፋፋ የሚያደርጉት “የውጭ ዜጎች ናቸው” ሲሉም ወንጅለዋል። ለዚህም ዓላማቸው “እርዳታን፣ ፖለቲካን እና ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ” ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እስከ 15 ዓመት በህግ እንደሚያስቀጣ ቢደነገግም መምህር ደረጀ ግን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይበልጥ የጠነከረ ህግ እንዲያወጡ አሳስበዋል። ስሙ ያልተገለጸ አንድ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አክቲቪስት ለአሶሴትድ ፕሬስ እንደተናገረው በኢትዮጵያ ለሁኔታው ባለው የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ምክንያት “ለደህንነቴ እሰጋለሁ” ብሏል።
Blogger Comment
Facebook Comment