“የሙሴ ጽላት በኢትዮጵያ መሆኑን የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ አለ” ይላል አሜሪካዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪ ቡድን

ከዚህ በፊት ግራሃም ሃንኮክ ጽላተ ሙሴ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ ፅፎ ነበር። አሁን ደግሞ ይህንን እውነት አሜሪካውያን ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል። የምዕራባውያን ምስክርነት ባያስፈልገንም። እውነት ማረጋገጣቸው በጎ ነው።

በታዋቂው አሜሪካዊ ተመራማሪ፡ በ ቦብ ኮርኑክ የሚመራው የመጽሐፍ ቅዱስአርኪኦሎጂ፡ የፍለጋ እና አሰሳ ተቋም(BASE) እንደገለጸውና እንደ ተቋሙ አጥኒዎች ምርምር ከሆነ፡ የሙሴ ጽላት ምናሴ በሚገዛበት ዘመን ከኢየሩሳሌሙ የቤተመቅደስ ተራራ ከተወሰደ በኋላ በግብጽ የአይሁዶች ግዛት ወደ ነበረችው የኤሊፋንቲን ደሴት እንዲያርፍ ተደረገ።
ከዚያ በኋላ፡ የአባይን ወንዝ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን መነኩሴዎች ብቻ ወደ ሚገኙባት የጣና ሀይቅ ቅድስት ደሴት፡ ወደ ጣና ቂርቆስ ተወሰደ።

ከዚያም በኢትዮጵያ በስተሰሜን ወደምትገኛዋ ወደ አኩሱም ከተማ ተዛውሯል።
የሙሴ ጽላት በተጨማሪም ሀያል እና ተዓምረኛ እንደሆነ የሚታመነውን እንደ የአሮን በትር የመሳሰሉትን ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕቃዎች እንደሚይዝ ይነገራል።

ይህ ዜና በአክሱም ጽዮን ሰሞን መውጣቱ በጣም የሚገርም ነው!!!

ጽዮን ማርያም – ዑራኤል – ጊዮርጊስ – ተክለሃይማኖት – መርቆርዮስ

"የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው"
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment