ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ታላቁን ንጉሣችንን፡ አፄ ምኒሊክን በማታለል ጂቡቲን እና ኤርትራን ከእናት አገራቸው ኢትዮጵያ የነጠለቸው፥ ብላም የማታለያና ጥገኛ የማድረጊያ የምድር ባቡር ከረሜላውን ለኢትዮጵያ የሰጠችው ፈረንሳይ በእሳት በመጋየት ላይ ነች። ወስላታው ማክሮን በሰሞኑ አመጽ ተረብሿል፣ ከሃሳብ ረሃብ የተነሳ በጣም ተጨንቋል፤ አሁን ከዚህ የጭንቀት ጉድጓድ ለመውጣት ጥረት እያደረገ ነው። የሽብር ጥቃት አቀነባብሮት ይሆናል። ሦስቱ "M"ች፤ ማክሮን፣ ሜርከል እና ሜይ፡ በሚሊየን የሚቆጠሩትን እስማኤላውያኑን ወደ አገሮቻቸው ያስገቡት እንደዚህ ባሉት የጭንቅ ቀናት እንደፈለጉት ሊጋልቧቸው ስለሚችሉ እንዲህ ሊጠቀሙባቸው ነው። የንጹሀኑ ህይወት ግድ አይሰጣቸውም።
በአገራችንም ከሞግዚቶቹ ትምህርት የወሰደው ግራኝ ዐቢይ አሕመድም ተመሳሳይ ድርጊቶችን በመፈጸም ላይ ነው። የመስቀል አደባባዩ ድራማ የሚጠቀስ ነው። እነዚህ ሉሲፈራውያን የንጹሀኑን ደም እንዳፈቀዳቸው በማፍሰስ ላይ ናቸው፤ ህፃናቶቻችንን በመመረዝ ላይ ናቸው። ባለፈው መስከረም ወር ላይ፡ የእነ ፈረንሳይን ትዕዛዝ በመቀበል አዲስ አበባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት የቆመውን የ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ኃውልት ካላፈረስን እያሉ ሲዝቱ የነበሩት የዋቄዮ አላህ ልጆች ባለፈው "ሰንበት" (ሰንበት መካሄዱ ያለምክኒያት አይደለም) በፈረንሳይ ከተቀጣጠልው ችቦ ትልቅ ትምህርት ፈጥነው ሊወስዱ ይገባቸዋል።
እምዬ ምኒልክ ካረፉ ዛሬ ታኅሣሥ 3, 2011 ዓ.ም. 105ኛ ዓመት ይሆናል። የዳግማዊ አፄ ምኒልክ መካነ መቃብር በአዲስ አበባ ከተማ ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት አጠገብ ባለችውና ለመታሰቢያቸው ትሆን ዘንድ ልጃቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ባሳነጿት በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ይገኛል። ሀገረ ፈረንሳይ ደግሞ በተቃውሞ እየነደደች ነው።
እጃችሁን ከሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ላይ አንሱ!
Blogger Comment
Facebook Comment