በዓለማችን ፡ በቁጥር አንድ ከሚታወቁት ፡ የህጻናት በጎ አድራጎት ድርጅቶች ፡ የአንዱ መሥራች ፡ ህጻናት በማባለግ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ !

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

                 

ፒተር ዳግሊሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [ሰይጣናዊና የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት] አማካሪና ዓለም አቀፍ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻነት መርጃ ድርጅት መሥራች፣ ከህጻናት ጋር ወሲብ በመፈጸም በሀገረ ኔፓል ባረፈበት ቤት ውስጥ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ውሏል። በቁጥጥር ሥር በሚውልበት ወቅት አብረዉት የ፲፪ እና ፲፬ ዕድሜ ያላቸው ህጻናት አብረዉት ነበር።

ፒተር ዳግሊሽ ፡ የ፷ ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ሲሆን የካናዳ ዜግነት ያለውብ በመላው ዓለም በመዞር ህጻናት በመርዳት ይሰራል። የሉሲፈር አገልጋዮች ኤዶማውያንና እስማዔላውያን በበጎ አድራጎት ሽፋን በሚከፍትዋቸው ድርጅቶች የዓለም ህዝብ በተለይ ኢትዮጵያውያንን ሥጋዊው ድህነታችንን ምክንያት በማድረግ ግብረሰዶምና ሌሎች እንግዳና ሰይጣናዊ የሆኑ ድርጊቶች በረቀቀ መንገድ እያለማመዱት ነው።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት [የነርሱ ሰይጣናዊ ድርጊት ደጋፊ ቢሆንም] ያጸደቀው የውጭ ማደጎ ክልከላ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል። ይህ ካልሆነ እነዚህ ሰላቢ እጆች ያዘጋጁልን ወጥመድ ውስጥ በቀላሉ ሊያስገቡን ይችላሉ።
ትጉሃን አባቶቻችን ለቸሩ እግዚአብሔር ሁሌ፡ለመሪዎቻችን ልቦና ስጣቸው፦እያሉ ይጸልያሉ።
ገብርኤልንም እግዚአብሔር አለው– “በዘፋኞችና በተናቁ ሰዎች ላይ÷ በአመንዝራ ልጆች ላይም ሂድ÷ የአመንዝራዪቱን ልጀችና የትጉሃንን [መላእክት ማለት እንደሆነ ይጠቅሳሉ] ልጆች ከሰው ለይተህ አጥፋቸው፡፡--- መጽሐፈ ሔኖክ ፫፡፲፩

ማክሰኞ ሰኔ 05, 2010 ዓ.ም.

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment