ኮሮና ቫይረስ ጎረቤታችን ኬንያ ደርሷል

ከአንድ መቶ በላይ ሰዎችን የገደለውና ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት እየተዛመተ ባለው ቫይረስ የተጠረጠረ አንድ ኬንያዊ ተለይቶ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ተገለጸ።

ከኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ጋር የሚመሳሰል ምልክቶች የታዩበት ይህ ኬንያዊ ተማሪ ለትምህር ቻይና ቆይቶ እንደተመለሰ ተነግሯል።

ተማሪው ከቻይና እንደተመለሰ የገዳዩ በሽታ የሚመስሉ ምልክቶች እንደታዩበት እንደታወቀ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዶ ከሌሎች ህሙማን ተለይቶ ክትትልና ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

 ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል የሆስፒታሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ህዝቅኤል ጊካማቢ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ተማሪ ከቻይናዋ ጓንግዡ ግዛት በኬንያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተሳፍሮ ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ጆሞ ኬንያታ አየር ማረፊያ መግባቱን ገልጸዋል።

በአየር ማረፊያው ውስጥም በበሽታው የሚያስጠረጥሩ ምልክቶች እንደታዩበት በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ መደረጉን አመልክተዋል።ይህ ከአደገኛው ኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አፍሪካ ውስጥ የተገኘ የበሽታው ሁለተኛው ተጠርጣሪ ሲሆን በኬንያ ውስጥ ግን የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስካሁን ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment