ፖለቲካ፣ ሃይማኖት እና ሣልሣዊ ቴዎድሮስ የፖለቲካ ማብቃት

✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

ነጮች የሣልሳዊ ቴዎድሮስን ጉዳይ ከእኛ ከሰረቁት መጻህፍት፣ በሌሎች ከተጻፉትም ተረድተዋል። የሣልሳዊ ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ባልሆኑ ድርሳናትም ተገልጿል።

የግብጽን ንጉስ ሽሮ፣ ሚስቱን ማርኮ፣ አባይን ገድቦ ግብጽን እንደሚያስገብር በራዕይ ሳቤላ ቢገለጽም፤ የግብጽ ራዕየ ሳቤላ ይህንን ክፍል አስወግዶታል። ፖለቲካ ከሃይማኖት በላይ እየሆነ ነው ዓለማችን የተበጠበጠችው፤ ፍቅረ ሥላሴ ሞገስ እንደሚሉት የሃይማኖት ልዩነቶች መንስኤው ነገረ መለኮት ሳይሆን ፖለቲካ ነው።

ግብጽ፦ ጋያ የሚያጨስ፣ መስኪዶችን ያስፋፋ፣ እንዲሁም ወደ እስልምና የተለወጡ ጳጳሳት ስትልክልን የነበረው ፖለቲካ ተጭኗት ነው። በአንድ ወቅት የግብጹ አረብ ንጉስ ለኢትዮጵያ ጳጳስ እንዲሾም በሚለው ሃሳብ ሲስማማ ግብጻዊው ፓትርያርክ ግን ግብጽ ግብር ይቀርባታል በማለት ሃሳቡን ውድቅ አድርገዋል። ከመጀመሪያውም ለኢትዮጵያ ጳጳስ ከግብጽ የመምጣቱ ነገር የፓለቲካ ሴራ ያለበት ነው።

ፖለቲካ ሃይማኖትን ተገዳድሯታል፤አይሁድ ክርስቶስን ያልተቀበሉት ትምህርቱን ከመቃወም የተነሳ ሳይሆን ከሮማ ግዛት ስላላወጣቸው ነበር፤ ቫቲካን ከኦርቶዶክስ የተገነጠለችው በነገረ መለኮት እውቀት በመበለጧ ክብሯ የነተካ መስሏት ነው፤ #ፕሮቴስታንት ከካቶሊክ የወጣው አሥራት ለሮማ መክፈል በተሰላቹ ሃገራት የተነሳ ነው፤ አንዳንድ ሃይማኖቶች ለፖለቲካ ግብ ሲባል ሆን ተብሎ የዘር ጥላቻ ተካቶባቸው የተመሠረቱ ናቸው። አሁንም አንዱን ብሔር ከጠሉ እሱ የማይከተለውን ሃይማኖት መቀበል ተለምዷል፣ የአሜሪካ ጥቁሮች ነጮቹን ለማበሳጨት ወደ እስልምና መግባትን አዘውትረዋል። የአፍሪካ ዜጎች የቅኝ ገዢዎችን እምነት አንቀበልም በማለት ወደ ባህላዊ እምነታቸው ሲመለሱ ይታያል። #ኢትዮጵያውያን ለአባቶቻቸው ያላቸውን ንቀት ለማሳየት ወደ ነጮች ሃይማኖት እየፈለሱ ነው።

የፖለቲካ መጻህፍት እንደ አውግስቲን ባሉ የነገረ መለኮት ሰዎች የተዘጋጁ ነበሩና ፖለቲካን ከሃይማኖት መለየት ከባድ እንደሆነ ይታወቃል። አንዳንድ ሃይማኖቶች በግልጽ ሃይማኖቱ ፖለቲካና አስተዳደርን ያካተተ እንዲሆን አድርገዋል። ሌሎች በፖለቲካ ጉዳይ አንገባም ብለው ራሳቸውን አግልለዋል። የኢትዮጵያ ነገሥታት ፖለቲካና ቅድስናን በማስተባበር የታወቁ ነበሩ፦ ኢትዮጵያም በመምሬ ዮሐንስ(Prestor John) ትርክት ትታወቃለች፤እርሱም ንግስና ከቅስና ያስተባበረ እንደሆነ ይነገራል። በቀዳማዊ ምኒልክ ቢከፍልም ከመልከጸዴቅ የመጣው አሠራር ክህነትንና መሪነትን ያዋኻደ ነበር።

የጌታ የማዳን ሥራ ከተሠራ በዃላ በተለያዩ አሻጥሮች ማዳኑ በሙላት እንዳይገለጽና ምድሪቱ እንዳትባረክ ሲሰራ ቆይቷል፤አንዳንድ እምነቶች በስውር ሌሎች በግልጽ ክርስቶስ እንዳላዳናቸው ይሰብካሉ፤ወንጌሉም እስከ ዓለም ዳርቻ ባለመሰበኩ ምድራችን የማዳኑ ሥራ ያልተሰራባት መስላለች።

"ይህ ወንጌል እስከ ዓለም ዳርቻ ይሰበካል፤ከዚያም መጨረሻው"ይሆናል ይላል የወንጌሉ ትንቢት፤እስካሁን የተሰበከው ትክክለኛ ባይሆን ነው እንጂ እስከ ዓለም ዳርቻ ወንጌሉ ያልተሰማበት የለም፤ሣልሳዊ ቴዎድሮስ የሃይማኖት ልዩነቶችን አጥፍቶ በዓለም በጠቅላላው እውነተኛው ወንጌል እንዲሰበክ ያደርጋል፤በእውነተኛው ትምህርት የተነሳ ምድሪቱ ለአርባ ዓመታት ፍጹም ተድላና ፍስሃን ታስተናግዳለች፤ከዚያ በዃላ ሰባት ነገስታት ይነግሱና ፍጻሜው ይሆናል።

አረቦች አገጩ ትንሽ ራሰ በራ ኢትዮጵያዊ ካዕባን ያፈርሰዋል ሲሉ ተንብየዋል፤የሣልሳዊ ቴዎድሮስ መምጣት ለአረቦች፣ ለአይሁድ፣ ለቫቲካን፣ ለአረሚዎች፣ ለግብጽ መልካም ዜና አይደለም።ሆኖም የሮማው ጳጳስ ውድቅ ተደርጎ የሮማው ንጉስና ሣልሳዊ ይስማማሉ፤ ሮማም እንደተለመደው ኢየሩሳሌምን ትይዛለች፤ሣልሳዊ የቀድሞ ግዛታችንን ግብጽን ይጠቀልላል። ኢትዮጵያዊው ንጉስ እስያኤል እሥራኤልን ለማስገበር ተንቀሳቅሶ ነበር ግን ሥላሴ ተው ብለው እንዳስቆሙት ተጽፏል። ኢትዮጵያ ኢየሩሳሌምን እንዳትይዝ ከጥንት የመጣ ግዝት ያለ ይመስላል።

ቫቲካን ኢትዮጵያዊውን ንጉስ ካሌብ የናግራን ክርስቲያኖችን በመታደጉ ከቅዱሳኗ ደምራዋለች፤ ቫቲካን ኢትዮጵያን ለማኮተለክ ጥራለች በዚህም ምክንያት ብዙ ደም ፈሷል፣በዃላ ደግሞ ሃይማኖታችሁ ከሃይማኖታችን ልዩነት የለውም የሚሉ መጻህፍት በኢትዮጵያውያን ኮተሊኮች እንዲታተሙ አድርጋለች፤አለቃ አያሌው ታምሩን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት "አንድ አይደለንም" የሚል መልስ ሰጥተዋል፤አለቃ አያሌው ታምሩ የጻፉት"መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና"የሚለው ድርሳን ውስጥ ልዩነታችን በግልጽ ተቀምጧል።

ሮማን አምርረው ከሚጠሉአቸውም ጸሃፊያን መካከል የኛዋ ዶ/ር መስከረም ለቺሳ አንዷ ናት፤የቫቲካንን ቅሌት እና ዓለምን ያወኩት ሴራ በመጽሃፉም በፊልሙም የገለጹ ነጭ ጸሃፍያን በርካታ ናቸው፤በስፋት የሚታወቀው ደግሞ ዳን ብራውን ነው፤የሣልሳዊ ሥራ የሮማን ሃሰትነት ግልጽ ከማውጣት ነው የሚጀምረው፤በሮማ ምክንያት የተከፋፈለው የክርስትና ሃይማኖትም ይሰባሰባል፤ሣልሳዊ ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጫና ከማውጣት ባለፈ ራሱ ፖለቲካን ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል፤ ምክንያቱም የሣልሳዊ አገዛዝ መላውን ዓለም የሚያስደስት ነው የሚሆነው፤ ፖለቲካ በታሪኳ እንዲህ ያለ ነገር አምጥታ አታውቅም የዓለም ፖለቲካ አንዱ ከአንዱ ነጥቆ የሚተኮስበት፣ አንዱ ሲወድቅ ሌላው የሚነሳበት የተራ አሠራር ነው።

ሣልሳዊ ለኢትዮጵያ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች፦ የኢትዮጵያን ዓለምን ያካለለ የቀደመ ገናንነቷን እና የቀደመችው ግዛቷን ግብጽን ማስመለሱ አንዱ ነው፤የግብጽ ጠላትነትም በዚህ ያከትማል፤አባይንም ይቆጣጠራል። በአጠቃላይ የከረሙ የኢትዮጵያን ቁጭቶችና ቅሬታዎች ያስወግዳል። ለሁሉም ያስቸገረውን ዘረኝነትን ይሽራል። ከዓለም ደግሞ ለብዙዎች እስካሁን ያልተቻለውን የተራ አሠራር  ይነቅላል፤ሃሳዊ እምነቶችን ለመለየት ለተቸገረው ዓለምም በግልጽ እውነተኛውን ከሃሰቱ እንዲለዩ ያስችላል፤የችግር ሁሉ ምንጯን ቫቲካንን ይረታል፣ረባሽ እምነቶችን ያስወግዳል፣ አይሁድንም ከዓለም መሪነት ያነሳቸዋል።

በአጠቃላይ በሣልሳዊ ቴዎድሮስ ግዙፍ ፖለቲካዊ ለውጦችን ዓለማችን ታስተናግዳለች፤ ለሁሉም ግን አስደሳች ጊዜ ይሆናል!!!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment