ያሬዳዊ ሥልጣኔ

✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያሬዳዊ ሲሆን የአውሮፓውያን ደግሞ ፋውስቲዝም ነው! ኢትዮጵያን ምስጢራዊ ሀገር ካደረጓት አንዱ የሠማያዊ ሥልጣኔ እርሾ ዛሬም ሥለ አልጠፋ ነው። የሺ ዘመናት ናፍቆታችን ከሥላሴ ዙፋን ሥር ማእጠንቱን ይዘን መቆም፣ ከደመና በላይ መብረር፣ ከመላእክቱ ጋር ባንድነት መዘመር፣ የሞትን መላእክ ማዘዝ፣ እርኩሳን መናፍስትን ማሰር፣ ሰማይን መገዘት፣ ፀሐይን ማቆም እና ከመንበሩ ሥር የሚፈልቁትን ፍትህ፣ እኩልነት፣ ፍቅር ወዘተ እንዴት በዚህ ተቃርኖአዊ ምድር ላይ መለማመድ እንዳለብን ስንለማመድ የፎስትን ምድራዊ ተቅበዝባዥ እውቀት ሳንረሳው አልቀረንም .....
በዚህም ምክንያት በዚያ ትውልድም ሆነ በዚህ ትውልድ ኢትዮጵያ ብዙ የማይገባትን ስድብ አስተናግዳለች ምእራባዊ የሀይማኖት መሠረት በመነሳት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ምልኩስናዊ ነው።

የሆነው ሆኖ ቅዱስ ያሬድ በአክሱም ከተማ በነገሥታቶችና በማሕበረ ካሕናት ተከቦ ጮማ መቁረጥ፣ በወርቅ ወንበር ላይ መቀመጥን ... አልወደደም ይልቁንም ሥልጡኗን ከተማ አክሱምን ንቋት ከሰሜን ተራራዎች ባሻገር ያለችውን ሰማያዊ ሥልጣኔን ወዶ ከራስ ዳሸን ተራራ ላይ በበረዶ ቤት ከአራዊት ጋር መኖርን ወደደ እንጅ...
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ በቅ.ያሬድና በአቡነ ተክለ ሃይማኖት የተቃኘ ነው። ምድራዊ ሆኖ መርቀቅ፣ ከመናፍስት ጋር ባአዲስ ዜማ መሠለፍ፣ ከፀሐይ በላይ በክንፍ መብረር፣ አንበሳን፣ ነብርን፣ ዘንዶን አገልጋያቸው ማድረግ፣ ከታላቁ ንጉሥ የመጨረሻ እራት ተጋባዥ ለመሆን ለመሆን መጠበብ፣ በእግዚአብሔር ፊት ሥልጡን መሆን... በሌሎች አለማት የሌለ እኛ ኢትዮጵያውያን ያዳበርነው ቢሆንም አሁን ላይ ግን ይህ ስልጣኔ በቁስ ሥልጣኔ እንደ ኋላ ቀርነት እየታዬ ቢሆንም የጊዜ ሁኔታ እንጅ የመጨረሻው እና ትክክለኛው የሠው ልጅ ሥልጣኔ ያሬዳዊ ሥልጣኔ ነው። ይህንን እውነት የሚያረጋግጡ የአደገው የኳንተም ፊዚክስ ደረጃ ላእላይ ሳይንስ እየመሠከረው ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መሆን ያለበት የተዋሕዶ ሥልጣኔ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው... መለኮታዊው ሥልጡንነት ከስጋዊው ስልጣኔ ጋር ሲዋሀድ የሁለት አለማት ባለርስት ያደርጋልና....


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment