እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ኢሉሚናቲ


ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

ዓለምን በጥበብ ያበራን - Illuminate ያደረግን የመጀመርያዎቹ ህዝቦች ነን:: እኛ ኢትዮጵያውያን:: ዓለምን በጥበብ ስናበራ መሰረታችን #እግዚአብሔር ነው:: የሚረዱን ደግሞ #ቅዱሳን መላእክት ነበሩ:: የኛ የቀደመ የብርሀን የስልጣኔ ዘመን በሰማያዊ ሀይላት እና በአያቶቻችን መካከል በተፈጠረ ህብረት አማካይነት የተመሰረተ ነው:: ስለዚህ ዛሬ ላይ ከወደቀው ከይሲ አዛዝኤል ጋር ህብረት ፈጥረው እኛ ነን Illuminati እኛ የስልጣኔ ብርሃን እያበራንላችሁ ነው ሲሉህ ማለት ያለብህ ወግድ ነው:: እናንተ ብርሀን አይደላችሁም ጨለማ ናችሁ ነው ማለት ያለብህ:: #እውነተኛዎቹ የብርሀን ሰዎች ጥንታውያኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው:: በቃል እንዳትታለሉ:: ከቃሉ ጀርባ ያለው ታሪክና ፍልስፍና እንዲሁም መልእክት ላይ ትኩረት አድርጉ:: አሁን ለምሳሌ ቅዱስ ንጉሥ ላሊበላ ሚስጥራዊ በሆነ የስነህንፃ ግንባታ ጥበብ ለዓለም ብርሀንን መለኮስ ችሏል:: ግን ዛሬ ላይ እኔ ነኝ ብርሀን የሚልህ የአዛዝኤል ዲቃላ የሆኑት ምእራባውያን የኛ ቅዱስ ንጉሥ የሰራውን ሰርተዋል? አልሰሩም:: ለምን? እውነተኛ ብርሀን አይደለማ:: ብርሀን ከእኛ ዘንድ ነበር የነበረው:: ዛሬ የጨለመብን የኛን ብርሀንን አጥፍተን የአዛዝኤል የድቅድቁ እውቀት ስር ስለተወሸቅን ነው:: ልዩነቱ በደንብ ይገባችኃል ብዬ አስባለሁ:: ከአዛዝኤል ጨለማ ወጥተን ወደ #ኢትኤል ብርሃናዊ ጥበብ እንመለስ!!!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment