✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
ኢትዮጵያ ቡናማ ቀይ የተራራ ሰንሰለቶች ያሉባት የምስራቅ አፍሪካ ፈረጥ ናት። ለበርካታ አመታት ስሟ ከሚስጥራዊነቷ ጋር የሚነሳ፤ ሁለነገራ ለሰወች ሩቅ የሆነች ምድር ...
ኮስሞስ ስለ እጣኗን ስለ ድንቅ ማዕድኖቿ የጻፈላት፤ ታላቁ አሳሽ እነ ሁዋን ቤርሙዴዝ፤ ክርስቶፈር ደ ጋማ፤ ጀምስ ብሩስ፤ እና ሄነሪ ሰልት፤ ህይወታቸዎን ለአደጋ በማጋለጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘልቀው ከበረከቷ ተቋድስዋል።...
አንድ ጠቢብ የከርሰ ምድር አጥኝ ሊቅ ሰው ፍለጋዬና እና መቃተቴን ያስተዋሉ የዘመናት ሚስጥሩን እፈታ ዘንድ በትውልድ ቅብብሎሽ የተገኘን ሚስጥራዊ ካርታን አሳዩኝ።
ሰባት ረቂቃን ቦታወች ተቀምጠዋል ..እኒህን ሚስጥራዊ ቦታወች ለ ሺ ዘመናት በከርሰ ምድር አጥኝወች ተመርምረዋል፤ በማዕድን ቆፋሪወች ተበርብረዋል፤ በአለማቀፍ በአሳሾች ታስሰዋል።
የካርታውን ጥብቅ ሚስጥር ለመፍታት...
ጅማሮዬን..በቀይ ባህር ዳርቻ በሚገኘው ኤርትራ የአፋር አካባቢ እንዳደርግ ካርታውን አስጨብጠው የትውልድ አደራውን አወረሱኝ። ...የካርታውም ቁልፍ ለመፍታት የሰለሞንን የማዕድን ሃብቶች እንደሚጠብቁ በአፈ ታሪክ የሚነገረውን በጂቦች የተወረረውን አካባቢ ሐረርን...የሚስጥራት ሁሉ ሙዳይ የሆነን በሰሜን ኢትዮጵያ ወዳለ አንድ ገዳም ይመራኛል..ሌላኛው ወደ ወሎ ይጠቁመኛል...
ምናልባት የእኒህ ሚስጥራዊ ቦታወች መገኘት አንድ ታላቅ የትውልድ እንቆቅልሽን ይፈታል...!
Blogger Comment
Facebook Comment