✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
ጥንት ህገ-ልቡናን ገንዘብ ያደረገቸው የአዳም የሱባኤ ምድር ኢትዮጵያ በደብረ-ቅዱስ ተራራ ግርጌ ያለቸው ኢትዮጵያ ብዙ ታሪክ አላት ከሰማነው ከተጻፈው ይልቅ ድንቅ ግዙፉ ሙሉ ንዑድ ክቡር የሆነ ታሪክም ጥበብ አላት ይህን ስልህ ወዳጄ ሀገሬን ያለ አግባቡ እያሞካሸዋት እንዳምሰልህ ይልቅስ ፍቅሯ እንደ እሳት በልቤ ቢንቀለቀል መናገር ግርም አለኝ እና ፍዝዝ ብየ ቀረሁ አየህ ወዳጄ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ፣ ታሪኳ ሲወሳ የሚያንገፈግፋቸው የሚያሽ የሚወቃቸው አይጠፉም! ከነዚህ ከእነዚህ የሙታን ስብስብ ይልቅ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ እና ሰላም ታጥቀው ደምቀው የቆሙት ብርቶች ናቸው ታዲያ እነዚህ ጠበብት ኢትዮጵያውያን ይባላሉ።
ምክንያቱም ጥበብ ማለት እግዚአብሔርን መፍራት እግዚአብሔር የሚፈራ ደግሞ ጥበበኛ ይባላል። ጥበበኛ ያሳደገው የጥበበኛ ልጅ ይባላል! ታዲያ እነዚህ ጥንት ኢትዮጵያውያን ጥበባቸውን አልቀበሩትም አልነፈጉንም! ለጋስ ቸር ብልህ አስተዋይ የእግዚአብሔር ሰው ስለሆኑ እንዳውም ክፉ ትውልድ አግኝቶት ከሚያጠፋት ይልቅ ደግ ትውልድ ሲመጣ እንደንጠቅምበት ከደህና ከከበረ ስፍራ አኖሩት! በክብር አክብረው ሌባ ከማይድርስበት ብል እንዳይበላው ከሚያደርግ ድንቅ ስፍራ አኖሩት! ዝም ብለው ማኖር ብቻ እንኳ አይደለም! ጠባቂ ትውልድ ቀመርን ቀማሪ ታሪክን አዋቂ ትውልድ አብረው እየመረጡ እንጂ ታዲያ ይህች ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ለፈቀደለት ዛሬም ትገለጻች። ።ላልፈቀደለት ግን ስውር ናት ትውልዱ ጠማማ ሆኖ እንጂ አባቶቻችንስ ደጎች ትሁታን ጸባየ ሠናይ ግብረ መልካም ናቸው...!!!!
Blogger Comment
Facebook Comment