✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
በርካታ ያልተነገሩ ያልደረስንባቸው ያላስተዋልናቸው ድንቅ ታሪክና ጥበቦች አሉን። እኒህ ድንቅ ታሪኮቻችን ከሀገረ ሰባዊ ማንነት በዘለለ አለማቀፊዊ ፋይዳ ያላቸው ፈላጊወቻቸውን እየፈለጉ ከተዳፈኑበት የዘመን አዙሪት የሚገልጣቸውን ትውልድ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
ከስሜታዊና ግልባዊ አካሂያድ ተላቀን ለአገርና ለትውልድ የሚተርፍ ድንቅ ታሪኮቻችንን ከተዳፈኑበት በማውጣትና ለአለም ለማሳወቅ አገራዊና ሃይማኖታዊ ሃላፊነት አለበን።
እኔ አንድ ብየ ጀምሬዋለሁ የአባቶቸን ጥበብ፣ እውቀት ፣ ሃይማኖታዊ ሆነ አገራዊ አሴትን፤ የልተነገሩ ድንቅ ታሪኮቻችን፤ መግነጢሳዊ ሐይል ያላቸውን ቦታወች፤ ስውራን ገዳማት፤ ሚስጥርን ያዘሉ የጥንት ብራናወች፣ ስለ ትላንትነ ማነነታችን በታሪክ፣ ስለ ምትወለደዋ የነገዋ አለም ደግሞ በራዕይ፣ የሚናገሩ ድንቅና እጹብ ዶክሜንቶች፤ ስለ አለፉት ጠቢባን አባቶች ጥበብ ታሪካቸው እንዲሁም የእወቀታቸውን ጥግ ለመግለጥ "ሀ" ብየ ጀምሬያለሁ።
#የአክሱም_ሃውልት እንዲሁ ተጠርቦ የቆመ ትልቅ ድንጋይ የሚመስለው ብዙ.. ነው። አብዛኛው ዘመናዊ ትምህርት ተምሬ ሳይንስ ገብቶኝ ሳይንቲስት ነኝ የሚለውም (ወይ መማር አያ ) እንዴት አቆሙት ከሚለው ያለፈ ጥያቄና ግርምት ያለው የለም።
የኔ ጥያቄና ግርምት ግን ብዙ ነው። እንዴት በዚህ ቅርጽ ሰሩት ለሚለው አርኪዮሎጂስቶች እንደሚሉት በመጥረብ ሳይሆን በማቅለጥ እንደሆነ ፍንጭ
አግኝቻለሁ። ግን ለምን ዓላማ? ሃውልቱ ላይ ያለውስ የተቆለፈ የሚመስል የበር ምስል..? ለምን ምክንያት? ስነ- ከዋክብታዊ ሚስጥር ይሆን? አሊያ ምናልባት ወደሌላ ዓለም (Another Dimension) መግቢያ በር ይሆን? .... መልስ አልባ የዘወትር ጥያቄዎቼ ናቸው። አንዳንዴ የችግራችን መፍትሔ እዚህ በር እና መሰሎቹ ላይ በሚስጥር የተቆለፈ ሁሉ ይመስለኛል።
በጊዜ ሂደት መለኮታዊ ጥብብ ከሰው ልጂ እየሸሸች እና እየራቀች አሁን ላለንበት ውስብስብ መለኮታዊ ሚስጥር ተዳርገናል።
ነገር ግን ባወቅነው ልክ ለመናገር በተረዳነውም መጠን ልንመሰክርና ታሪክን ልንመረምር ይገባል!
ከ 889-869 ከክረስቶስ ልደት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል አብሪ ኮከብ የሆነች በአለም ተጽኖ ፈጣሪ ታላቅ እና ገናና የንግድ ከተማ በታላቁ ንጉስ አክሱማይ ራሚሱ እንደተመሰረተች የታሪክ ድረሳናት ይናገራሉ።
የአክሱም ከተማ ለዘመናት የሕዝብ መኖርያ ብቻ ሳትሆን ዛሬም ድረስ አለም ላይ የደመቁ የሥነ-ጽሁፍ፣ የሥነ-ሕንጻ የቅርጻ ቅርጽ ሥዕላት እንዲሁም የታላላቅ ገዳማት መገኛ አሁን ላለንበት ሰፊ የክርስትና አማኝ መገኘት ሚናዋ ከፍተኛ ነበር።
ታዲያ ከታላቋ አክሱም ስር ብዙ ያልተተረከ ሀብት፣ ያልተነገረ ጥበብ፣ ያልተገለጠ ማንነት፣ ዘመንን እያስረጀ ትውልድን እየገፋ የሚኖር፣ የሚታይ ግን ያላስተዋልነው፣ ፊቷን እንጂ ልቡን ያልመረመርነው፣ ተዝቆ የማያልቅ ሚስጥራዊ ዶሴን በተገለጠ ሀውልት ያልተገለጠ ሚስጥሩን እንመርምረው ዘንድ ጉዞአችን ወደ አክሱም ሐውልት ይሁን።
የታነጸበት ዘመን በተለያየ ጻህፍት የተለያዩ ሐሳብ አለ አንዳንዶች ከ 3ኛው -4ኛው መቶ ክፈለ ዘመን ሲሉ፤ በሌላ በኩል የአክሱም ስረው መንግስቷ ሲመሰረት እንደታነጸ ይናገራሉ ይህም ማለት 546-532 ዓ.ዓ የ3ሺ አመት እድሜ መሆኑ ነው።
በቂ ጥናት መደረግ ቢገባው ካለው ነባራዊ ሁነት እና ከታሪካዊነቱ አንጻር በብዙ የሚያ ስማማው የ3ሺ አመት እድሜን እንደያዘ መሆኑ ነው።
ታላቁ የአክሱም ሐውልት 33 ሜትር ከፍታ ክበደቱ ደግሞ 520,000 ኪ/ግ ነው።
ስለ ታላቁ የእክሱም ሐውልት አገነባብና አቋቋም ብዙ አወዛጋቢና አከራካረ ነገሮች በየ ዘመናቱ በተነሱ ጠቢባኑ ይካሄዳል። ይህ አወዛጋቢነቱ ዛሬም ለ አርኪኦሎጂስቶች እና ለህንጻ ባለሙያወች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። አንዳንዷቹ ከተገነባበት ዘመን አንጻር የሰው ልጂን ንቃተ ህሊና ታሳቢ በማድረግ በሰወች እንኳን ሊሰራ ሊታሰብ አይቻለም ይላሉ። ታድያ የእዚህ ሐውልት ሰሪወች የቀደሙ ሐያላን ርኦይት ወይም ግዙፍን ወይንም ከሰማይ የወረዱ ኔፍሊሞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
በእርግጥ የሰው ልጂ ልብሱ ሰርቶ መልበስን በማያውቅበት የደንጋይ ዘመን ይህንን የመሰለ ዘመን ተሻጋሪ ሐውልት መስራት መቻሉ ጥያቄ ውስጥ ይጥላል።
ዛሬም ድረስ ይህ ሐውልት በጥንታዊየቱ ከአንድ ወጥ አለት መሰራቱ በአለም የሚመጥነው የሚተካከል አለመኖሩ በዛን ዘመን በሰወች ተገነባ ብሎ ማሰብ ይከብዳል።
ታድያ ይህ ሐውልት የተቀረጸው በምን አይነት መሳሪያ ነው...?
ይህ የአክሱም ሐውልት ለመቅረጽ የተገለገሉበት መሳርያ እብነ አድማስ ይባላል ታድያ ይህ ታምራዊ መሳርያ አለትን እንደ ሰም የሚያቀልጥ ጽነ ማዕድን ነው።
''ወአምጽኡ ሎቱ እብነ አድማስ ወወሀብዎ ወይቤልዎ ሑር ምድር ወንበርታ ወሕንጽ በኀየ ቤተክርስትያን''
''አብርሐና አጽብሐ በዚያን ጊዜ እብነ አድማስ አምጥተው ሰጡትና ወንበርታ ወደ ሚባል ሀገር ሂደህ በዚያ ቤተክርስትያን ስራ አሉት'' ይላል ገድለ አብርሐ ወአጽብሐ.... ይህ ማለት እብነ አድማስን እውነትም ለህንጻ አገልግሎት ሲጠቀሙበት እንደ ነበር ያሳያል።
ታላቁ ጥበብ እንዴት 33ሜትር ቁመት 520,000 ኪሎ ክብደት የሚመዝንን ግዙፍ ሃውልት ሊቆም ቻለ የሚለው ነው?
የቆመበት ሚስጥር ምንም በውል ባይታወቅም ጥበባዊ በሆነ መንገድ በነፋስ አውታር እንዳስቆሙት አበው ይናገራሉ።
ይህ ካልሆነ ምን አይነት ጥበብ ተጠቅመው ይሆን?..
ከዚህ ሃውልት ስር የሚገኝ ህንጻ መኖሩ ደግም ለሚሰማና ለሚያየው የሚደንቅ ነው።.....ይህ ድንቅ ሃውልት ከሃያላኑ የፒራሚድ ገነቢወች ጋ የሚያገናኘው ነገርም እንዳለ ይነገራል።
በአንዳንድ መዛግብት ላይም ከሃውልቱ ራስ ታምራዊ የሚያበራ ብርሃን እንደነበር እና ብዙ የሚደነቅ ታምራት ይታይበት እንደነበር ከሃውልቱ የተነሳበትና የጠፋበት ሁኔታ ከተነሳ በኋላም አሁን ያለበት ቦታ በብዙሃኑ ዘንድ ጥያቄን ይፈጥራል ....
ይህ ሃውልት ከአስደናቂ ስነ-ህንጻው ይበልጥ ጥብቅ እና የጠለቀ ሚስጥራዊ ኮድን ይዟል... ሐውልቶቹ የተቀረጹበት መንገድ ከልማዳዊ የህንጻ አሰራር ባሻገር የተለየ መልእክትን የያዙ ይመስላሉ....በእኒህ ሐውልቶች ላይ የተዘጉ በርካታ ከአለት የተቀረጹ በሮች በፎቅ መልክ ተደርድረዋል።
ይህ የተቆለፈ የድንጋይ በር ከፋቹን እስኪያገኝ ጥበባዊ ማንነቱን ለመግልጽ ፈቃደኛ አልሆነም እንደውም ጠቢባኒ ቅኔያዊ በሆነ መንገድ ታላቅ መልእክትን በዚሁ በተቆለፈ የአለት በር እያስተላለፉ ይመስላል...
ዛሬም ቆመው ከሚታዘቡንም ሆነ ወድቀው ከሚያስለቅሱን የአክሱም ሐውልቶች ላይ በበር ቅርፅ የተሰሩ የድንጋይ በሮች እና በነሱም ላይ ተደራራቢ የሆኑ ፎቆች ሚስጥራዊ የቁጥር ውክልናን ይዘው በዝምታ ለሚያልፈው የትውልድ ጅረት የሚናገሩት ሚስጥር እንደነበር እናያለን:: እነዚህ የድንጋይ በሮች የተቆለፉ ይመስላሉ:: በበር ቅርፅ እስከተሰሩ ድረስ የሚከፍታቸው ሆነ በሥራቸው የሚያልፍ ትውልድን የሚጠብቁ ለመሆናቸው እርግጠኞች ልንሆን ይገባል::
ያለ ምክኒያት በር አይሰራም፤ በሩም ከፋቹን እስኪያገኝ በሃያል እና በጥበቢባኑ ዘመን የተዘጋዉ ሚስጥር ከሶስት ሽ አመታት በኋላም የተዘጋውን የሚከፍት ሃያል እና ጠቢባኑን ትውልድ ይፈልጋል..... የተዳፈነችው ጥበብ ራሷን ጥገለጥ ዘንድ በር ፈላጊ ናትና ትቤ ምእታው አክስው መኑ አንተ ትላለች ? ....
የበሮች ሚስጥራዊ ኮዱን ቀጣይ እንመለከታለን..!
''ትቤ ምእታወ አክሱም መኑ አንተ.. .?''
(የተዘጋች የሆነች) የአክሱም በር (ትክፍትልህ ዘንድ) አንተ ማነህ ትላለች...
Blogger Comment
Facebook Comment