በአለም ላይ ለመጀመርያ ጊዜ የኤሌትሪክ ሀይልን የፈጠሩ ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን


ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

በአለም ላይ ለመጀመርያ ጊዜ የኤሌትሪክ ሀይልን የፈጠሩ ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ዶክተር ዱራሲላ ጁነዲ ሂውስተንን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካን ጥንታዊ ታሪክ ያጠኑ ምሁራን በመፅሀፎቻቸው  ላይ መስክረዋል።  ታዲያ ይህን የእነርሱን ንድፈ ሀሳብ ሊደግፍ የሚችል መረጃ አለን። ሁለት መፅሐፍት አሉ መፅሐፈ ብርሐን እና መፅሐፈ ፀሐይ ይሰኛሉ።

መፅሐፈ ብርሃን ብርሀን ለመፍጠር ከብርሀን ደግሞ ሌላ ሀይል ለመፍጠር ይገለገሉበት እንደነበር በትውፊት የመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ መፅሐፍ እዚህ ገዳም አለ እዚያ ገዳም አለ ከመባሉ ውጪ አሁን በቅጡ የሚገኝበት አይታወቀም አንዳንድ ሰዎች እንደውም በጀምስ ብሩስ አማካይነት ከጎንደር እንደተሰረቀ ይናገራሉ። መፅሐፈ ፀሐይ ደግሞ ስለ ፀሐይ ስለ ጨረቃና ከዋክብት ተፈጥሮ፣ ባሕሪ እና እንቅስቃሴ በቁጥር ስሌት የሚያስቀምጥ መፅሐፍ ነው። ይህ መፅሐፍ ለዘመናዊ የሂሳብ እና የፊዚክስ እንዲሁም ስነ-ከዋክብት ጥናት መሰረት መሆኑ የሚታበል ሀቅ አይደለም። እነኚህ መፅሐፍት ከክርስቶስ ልደት በፊት የተፃፉ እንደሆኑ ሊቃውንት ይናገራሉ።።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment