እኛ ኢትዮጵያውያን ቋንቋችን ከመንፈሳዊ ማንነታችን ጋር የተቆራኘ አንድምታ አለው። ለዛም ነው ኢትዮጵያዊ ጠይምነቱን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለወጥም ተብሎ የተነገረን። የግዕዝ ቋንቋ ቀዳሚ እንደመሆኑ አንተ የምትጠቀምበት ቋንቋ ተገልብጦ የተወሰደው ከኛው ፊደላት ነው። አንዱ ማስረጃ ነው ዋው የተሰኘው ቃል። ይህ ቃል ለኛ ለኢትዮጵያውያን ጥልቅ መንፈሳዊ ፀጋና አንድምታ አለው አንተ የምትጠቀምበት ቋንቋ ባለቤቶች ግን ይህን ቃል ሲገለብጡ ያለውን ሃይል ሳይረዱ በመሆኑ አሁኑም የአገሬን ሰው ትርጉም እንዳይረዳ መሰናክል ሆነውበታል። ስለዚህ የቃሉን መሰረታዊ ትርጉም መረዳት ስላለብን ሐዋርያው በስብከቱ እንተነጋረው እኛም ከላይ የፃፍነውን ፃፍን።
መዝሙር118(119) አሌፍ , ቤት, ጋሜል, ዳሌጥ, ሄ, ዋው, ዛይ, ሔት, ጤት, ዮድ, ካፍ, ላሜድ, ሜም, ኖን, ሳምኬት, ዔ, ፌ, ጻዴ, ቆፍ, ሬስ, ሳን, ታው በሚል ተፅፎ እናገኘዋለን።
"ዋው" [Wow] ከግእዝ ቋንቋ ተወስደው ከባእድ ቁዋንቁዋ ጋር ተደባልቀው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙት ቃላት መካከል "ዋው" [Wow] አንዱ ነው። #ዋው ከእግዚአብሄር አምላካችን ህቡእ ስሞች መካከል አንዱ ሲሆን #ትርጉሙም እግዚአብሄር በመንግስት፣ በስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በባህሪ አንድ የሆነ ማለት ነው።
ዛሬ ግን ትውልዴ እንግሊዘኛ መደባለቅ ፋሽን መስሎት በረባውም ባረባውም Wow የሚለው ወገኔ ባልተገባ ቦታ የአምላኩን ስም በመጥራት እግዚአብሄርን እያሳዘነው እንደሆነ በተረዳ ነበር።
" ዋው አቤቱ እንደ ቃልህ ምህረትና መድሀኒት ይምጡልኝ በቃልህ ታምኛለሁና" እንዳለ ዳዊት በመዝሙሩ!!!!
Blogger Comment
Facebook Comment