ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
[ኢትዮጵያ አውታር ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ] - ጀግናዋ ኢትዮጵያዊ እኅተማርያም ፡ እንዴትኮ አንጀቴ እንደምታርሰው። የምታስተላልፈው መልዕክት የውስጤን ስለሆነ ደስ ይለኛል።
ወገኖቼ ! ከወስላታ ካድሬ ዲያቆንና አገልጋይ ነኝ ባይ ተደማሪ ነፃ የምንወጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም
በቁጥር ፴፱ ላ ባስተላለፈቺው መልዕክት ይኽንን ብላለች።
☞ዶ/ር አብይ ጥምቀትን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ፀረ-ተዋሕዶ ነው።
☞ዶ/ር አብይ የተናገሩት እንኳን አንድ አገር እመራለሁ ከሚል ሰው፤ ከአንድ ምዕመን እንኳን የማይጠበቅ ነው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸውጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ማለታቸው፤ ሃይማኖታችን ጠፍቶ ሁሉ ነገር እንደ ፌስቲቫል እንዲሆን ነው።
☞ዶ/ር አብይ የተናገሩት እንኳን አንድ አገር እመራለሁ ከሚል ሰው፤ ከአንድ ምዕመን እንኳን የማይጠበቅ ነው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸውጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ማለታቸው፤ ሃይማኖታችን ጠፍቶ ሁሉ ነገር እንደ ፌስቲቫል እንዲሆን ነው።
☞ ለምንድን እራሱን የመቻል ብቃት ያለው ቅዱስ ታቦት ነው በታጠቁ ወታደሮች ታጅቦ እንዲሄድ የሚደረገው? ምን ዓይነት ቅሌት ነው?!
☞ አብይ አህመድ ኦርቶዶክስን ወዴት እየወሰደው ነው?የሚለውን ጥያቄ ሁሉም ሰው ሊጠይቀው የሚገባው ነገር ነው። ወዴት ወዴት ፎቀቅ እያልን ነው?ሃይማኖቱን ሁሉ ጨምቀው አንድ ሃይማኖት ለመፍጠር እየታገሉ ነው፤ አባቶች ስለዚህ ጉዳይ መናገር ይጠበቅባቸዋል።
☞ትናንትና ስልጣን ላይ የወጣ ሰው እንዴት ይህን ያህል ተዋሕዶን ደፍሮ ሊናገር ቻለ?!
ቃለ ሕይወት ያሰማለን፤ እኅቶች እና ወንድሞች፤ ጀግኖች! ምን አለ እያናዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ እንደ እናንተ መሆን ቢችል! ቸኩለው “አብይ አብይ” ሲሉ የነበሩት የአንዳንድ አባቶች ዝምታ ያደነቁራል። እየተካሄደ ስላለው ነገር እንዴት ዝም ማለት ይቻላል?
ዔዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያኑ ሕዝባችንን ከውስጥ እስከ ውጭ አብጠርጥረው አጥንተውታል፤ ቀስ በቀስ በማለማመድ ሕዝባችንን ፀረ–ክርስቶሱን እንዲቀበል ለማድረግ ማዘጋጀት ከጀመሩ ቆይተዋል። ምን እንደሚፈልግ፣ ምን መስማት እንዳለበት፣ ማንን መቀበል እንደሚችል በደንብ አውቀውታል። ስለዚህ ሕዝባችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ይችሉ ዘንድ ሰዎች እራሳቸው ፈቃደኛ ሆነው መርዛቸውን እንዲቀበሉላቸውና የፈጠሩት አጋጣሚም እንዳያመልጣቸው አሁን በጣም በመጣደፍ ላይ ናቸው።
ልክ ከዚህ በፊት ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም እና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳደረጉት እነ ዐቢይ አሕመድ አሊም (ስሙ ላይ በደንብ እናተኩር፤ ቍልፍ ሚና ይጫወታልና) በሲ.አይ.ኤ እና ኤፍ.ቢ.አይ እንዲሁም በእንግሊዝ የስለላ ድርጅቶች አማካኝነት ስልጠናን አድረገዋል። እነዚህ ድርጅቶች የ666ቱ ዋና ተዋንያን ናቸው። መሪዎቻችን የእነርሱን ትዕዛዝ መቀበል አለባቸው።
እነ ዐቢይ አኅመድንና አቶ ለማ ለገሰን ሰልጣን ላይ ለማውጣት የወሰኑት ገና ከ፳፯ ዓመታት በፊት ነበር፤ ኦነግ የኢሕአዴግ መንግስትን ለቅቆ እንዲወጣ የተደረገው በሉሲፈራውያኑ ዕቅድ ነው፤ ምክኒያቱም፡ ፩ኛ. በቋንቋ የተከፋፉሉ ክልሎች ተመሥርተዋል፤ “እስከ መገንጠል” የሚለው ሕገ መንግስት በመጽደቁም ግቡን መትቷል፣ ፪ኛ. የመስተዳደሩን ኃላፊነት በተለይ ለትግርኛ ተናጋሪዎች በማስረከብ የተዋሕዶ የጀርባ አጥንት በሆኑት ትግሬዎች ላይ መጥፎ ስም በመስጠትና በመኮነን ሕዝቡ ጥላቻ እንዲኖረው ለማድረግ ይችላሉና ነው። በ፳፭ ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና ሁኔታ መረዳት የማይችል አንድ ትውልድ ተፈጥሯልና። ይህን አሁን በተከታታይ በግልጽ የምናየው ነው።
ኢትዮጵያውያን መስማት የሚፈልጉትንና ማየት የሚመኙትን ድራማ እንዲነግሯቸውና እንዲያሳዩአቸው እነ ዐቢይ አሕመድ መረጡ፤ ግን እነርሱን በደንብ ከማስተዋወቃቸው በፊት፡ ሉሲፈራውያኑ ያዘጋጇቸው ምሁራኑ እና መገናኛ ብዙሃን “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” አሉ (መንግስቱ ኃይለማርያምም “ያለምንም ደም፤ ኢትዮጵያ ትቅደም! እያለ ነበር ሥልጣን ላይ የወጣው) ፣ “ባንዲራችን ላይ ኮከቡ መስፈሩ ተገቢ ነው አይደለም ” እያሉ የመረጧቸውን ሰዎች በማወያየት ኢትዮጵያውያንን አጠኑ፤ ሕዝቡ የት ድረስ አብሯቸው ሊጓዝ እንደሚችል ተገነዘቡ።
በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተጠሙ አገር ወዳዶቹ ኢትዮጵያውያን በየዋህነት “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” የሚለውን መፈክር አብረው ማሰማት፣ ኮከቡ ያላረፈበትንም ባንዲራ በየአደባባዩ ይዘው በመውጣት መፈንደቅ ጀመሩ። አሁን ይህ አገር ወዳድ የሆነው ኢትዮጵያዊ፡ ልክ፡ ቀደም ሲል “ነፍጠኛ” በማለት አማርኛ ተናጋሪውን ሲኮንኑት እንደነበረው፤ አሁን ደግሞ “ወያኔ” በማለት ትግርኛ ተናጋሪውን መኮነን እንዲበቃ ተደረገ፤ አንጎሉ ታጠበ። “ነፍጠኛ” እና “ወያኔ” የሚሉት የመወንጀያ ቃላት መግቢያ ሆኖ ለ “ተዋሕዶ ክርስቲያኖች” የተሰጡ የምስጢር ስያሜ ናቸው።
የእኅተማርያም ማሕበር አባላት ግሩም በሆነ መልክ በትክክል ጠቁመውታል፤ ኮከቡ ያላረፈበትን ባንዲራችንን በየቤተክርስቲያኑ መሰቀል ጀምረው ነበር፤ አሁን ግን ሁሉም ኮከቡን እንደገና እንዲለጥፉ ታዘዋል።
ዐቢይ አሕመድ ሥልጣኑን በተረከበ ማግስት፤ “እውነት ሕዝባችንን ለማገልገል የመጣ ሰው ከሆነ እነዚህን ሦስት ነገሮች በፍጥነት መፈጸም ይኖርበታል” ብዬ ነበር፦
- ፩ኛ. በቋንቋ የተከፋፈልውን የክልል ሥርዓት እንዲያፈርስ
- ፪ኛ. ኮከቡን ከባንዲራችን ላይ በአዋጅ እንዲየነሳ
- ፫ኛ. ከአረብ አገሮች ጋር ያለንን ጥብቅ ግኑኝነት እንዲያላላ
ዓመት ሆነው፤ ግን ሦስቱንም ጉዳዮች እስካሁን ለማስተካከል ሙከራ አላደረገም፤ እንዲያውም ሁኔታዎችን ወደ ባሰ መንግድ እየመራቸው ነው፤ በዚህም ሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን፣ አረቦችና የተባበሩት መንግስታት ፈላጭ ቆራጮች ታይቶ በማይታወቅ መልክ እያጨበጨቡለት ነው። ይህም በጣም ስላደፋፈረው፡ መጀመሪያ በትግርኛ ተናጋሪዎች ላይ ሤራ መጠንሰስ ጀመረ፤ አሁን ደግሞ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዞረ። አቤት ድፍረት!
የእኅተ ማርያም እኅቶችና ወንድሞች ያሉት ትክክል ነው፤ ሁኔታዎችን በደንብ የሚቃኝ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ ሊወስደው የሚገባው ግንዛቤ ነው። አዎ! ዶ/ር አብይ እና አጋሮቹ የ666ቱን ማህተብ ካልተቀበሉ በቀር ሥልጣን ላይ አይወጡም፤ አይቆዩምም። ሥልጣን ላይ ከወጡ ደግሞ የሉሲፈራውያኑን ትዕዛዝ መቀበል ግድ ነው፤ አሻፈረን ካሉ የመለስ ዜናዊ ዓይነት ዕጣ ስለሚደርሳቸው ይፈራሉ፤ ስለዚህ ፀረ–ኢትዮጵያ፣ ፀረ–ተዋሕዶ የሆነውን አጀንዳ የማራመድ ግዴታ አለባቸው ማለት ነው። እንደነርሱ ከሆነ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነችው ተዋሕዶ መጥፋት አለባት፤ እርሷ ከጠፋች የአንድ ዓለም ሃይማኖት እና መንግስት መመስረት ይቀላቸዋል።
ግን አይሳካላቸውም፤ ወዮላቸው! ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር አምላክ አንድ ባንድ ተንትኖ በኋላ ያሳያቸዋል። እነርሱን አያድርገን!
አዎ የሚያምን ከማያምን ጋር ምንም ሕብረት ሊኖረው አይገባም፦
[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥ ፲፬፡ ፲፭]
“ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?„
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥ ፴፬፡፴፮]
“በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።”
ስለ የተለጠፈበት ቀን
Blogger Comment
Facebook Comment