ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የኤሚራቶች መገናኛ ብዙኃን እንደጠቆመው ከሆነ፤ ባለፈው ዓርብ በተካሄድው የዱባይ ማራቶን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር የሰጣቸውን የኢትዮጵያን ካርታ በመያዛቸውና “ኤርትራውያን” የተባሉትን ወገኖች በማስቆጣቱ “ኢትዮጵያን የሚወክለው” ቆንስላ ይቅርታ ጠይቋል።
እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ የጠቀሳት የመጀመሪያዋ ሃገር ኢትዮጵያ ናት፦
[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፪፥፲፫]
“ የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።”
እግዚአብሔር አምላክ ፤ ኤርትራ፣ ጂቡቲ ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ ፣ ኬኒያ ወይም ኦሮሚያ የሚባሉትን ቦታዎች በጭራሽ አያውቃቸውም። እነዚህ ስሞች ሁሉ ኤዶማውያኑ ምዕራባውያን ያወጡላችሁ የማታለያ ስሞች ናቸው። እግዚአብሔር እነዚህን ቦታዎች የማያውቃቸው ከሆነ ለእነዚህ ቦታዎች ሰንደቅ ዓላማ ይዛችሁ የምትወጡትንም ከሃዲዎች አያውቃችሁም፤ በስንዴ መካከል እንደተዘራችሁ እንክርዳድ ናችሁና። አቤት ጉዳችሁ!
ኢትዮጵያውያን እን´ድንባት ዘንድ ፈጣሪአችን የሰጠንን እና የተረፈችውን አንዲት ኢትዮጵያ የሚያሳይ ካርታ ይዘው በመውጣታቻው የኢትዮጵያ መንግስት “ኤርትራውያን” ለተባሉት ወገኖቻችን በኢንግሊዝ የኢትዮጵያ ቆንስላ ይቅርታ መጠየቅ አይገባውም ነበር።
እንዲያውም ለኢትዮጵያውያን ነበር ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት፤ “የኦሮሞ” ነው የተባለውን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው በወጡት ከሃዲዎች ተግባር መሆን ነበር ማዘን የነበረበት።
ኧረ ወገን ተማሩ! በኤርትራ ላይ ላለፉት ፳፭ ዓመታት ከደረሰው መቅሰፍት ልምድ ውሰዱ!
Blogger Comment
Facebook Comment