ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ምዕራባውያን በጥቀር ህዝቦች ላይ የሚያደርሱት ግፍ ተነግሮ አያልቅም። የቀድሞው የተባብሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊን፤ የስዊድናዊውን ዲፕሎማት ሃመርስጆልድ አሟሟት አስመልክቶ አንድ በዴንማርካዊ ፊልም ሠሪ የተሠራ ጥናታዊ ፊልም በ “ሳንዳንስ ፊልም ፊስቲቫል” ላይ ባለፈው ቅዳሜ ቀርቧል።
በዚህ ‘Cold Case Hammarskjold,’ በተሰኘው ፊልም፤ እ.አ.አ በ 1961 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊን የገደሉት በእንግሊዝና አሜሪካ የስለላ ድርጅቶች የሚደገፉት ነጭ የደቡብ አፍሪቃ ቅጥረኞች እንደነበሩ ተጠቁሟል።
በዚህ አያበቃም፤ ከእነዚህ እርኩስ ቅጥረኞች ያፈነገጠው ግለሰብ አሁን በተጨማሪ እንደጠቆመው ከሆነ እነዚሁ የሲ.አይ.ኤና አባሮቹ ቅጥረኞች የደቡብ አፍሪቃን ጥቁር ሕዝቦች ለመጨረስ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ የሚያሰራጭ መርፌ ሆንብለው ይወጓቸው ነበር።
በእነዚህ ሉሲፈራውያን እየተሠራ ያለው ሥራ ለጆሮ የሚቀፍ ነው፤ ህሊና ላለው ተቀባይነት የማይኖረው ዲያብሎሳዊ ተግባር ነው። በአገራችንም እህቶቻችንን እና ሕፃናቶቻችንን በመከተብና በመመረዝ ላይ ናቸው።
እስኪ ይታየን፤ ሰው አገር ሄደው፣ እነርሱ አምላክ ሆነው በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠርውን ፍጥረት ለማጥፋት ይህን ያህል ሲተጉ፤ ምን ዓየነት እርኩሶች ቢሆኑ ነው እነ ሲ.አይ.ኤ. ኤፍ.ቢ.አይ እና ኤም.አይ.ፋይቭ?!!! ልክ እንደ መሀመዳውያኑ፡ ይህች ዓለም ለእነርሱ ብቻ ናት፤ ብቻቸውን ሊኖሩባት ይሻሉ።
የፍትሕ ጩኸት ጽዋ በእግዚአብሔር ፊት ሞልቶ ፈሷል። የአብርሃም፣ ይስሃቅና፣ ያዕቆብ አምላክ ፈጥኖ ለውርደት ያብቃቸው። ይኽ ሰይጣናዊ እኩይነት፣ በእግዚአብሔር ላይ የታወጀ፣ ሆኖም ሊያሸንፉት የማይችሉት ጦርነት ነው። እግዚአብሔር አይቻለሁ ብሎ በፍርድ ተንስቷል!
[ የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፩፥፰]
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።
[ ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፥፩፤፪ ]
“ መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው! ”
Blogger Comment
Facebook Comment